ፋልስ-yabeto

ፋልስ

Regular price
$4.00
Sale price
$4.00
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

በ1970ዎቹ መባቻ ዐሥራ ስድስተኛ ዓመቱን እንዳከበረ ነበር፤ በዚያ የሽብር ዘመን ከቤት የወጣው። በአፋር ምድር ሚሌ፥ ዲትባሕሪ፥ ታንጋየኩማ፥ ዱብቲ የተባሉ ቦታዎች ሠርቷል፡፡ በጥጥ ለቃሚነት በኪሎ 7 ሳንቲም ሒሳብ በቀን እስከ 25 ኪሎ የለቀመበት፤ በቀን 1.92 ሳንቲም እየተከፈለው በግንበኛነትና ቀለም ቀቢነትም የሠራበትም ጊዜ ነበር።
ቋሚ ሠራተኛ ሲሆን ከዳታ ኦፊሰርነት፤ የሰው ኃይል ልማት አስተዳደር እስከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊነት አገልግሏል። የሠራተኞች ማኅበር ሊቀመንበር በመሆንም የሠራተኞችን መብት አስከብሯል። በአዲስ አበባ አስተዳደር መካከለኛው እርከን የሰው ኃይልና የማስፋፊያ ፕሮጀክት ማናጀር ሆኖ ሠርቷል። በፍሪላንሰር ለአገር በቀልና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በግል አማካሪነት ሠርቷል። በመሬት አስተዳደር የሦስት ከተሞች (ማለትም ባሕርዳር፣ ድሬዳዋና መቀሌ) አስተባባሪ ሆኖም (ተቀማጭነቱ ፊንላንድና ጃፓን ለሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት) አገልግሏል፡፡ የግል አማካሪ ድርጅት ውስጥ በፕሮጀክት ጥናት ባለሙያነትም ሠርቷል። በፍሪላንሰር ሲሠራ በርካታ የኢትዮጵያ ክፍሎች ላይ ተዘዋውሮ የተለያዩ ጥናቶችን አድርጓል።
ከመስከረም 1/2013 ዓ.ም ጀምሮ ጡረታ ቢወጣም፥ ካለው የሥራ ልምድና ብቃት ተፈላጊነት ጋር አሁንም በኢስት አፍሪካ ሆልዲን የሪከርድ ማኔጅመነት ሲኒየር ኤክስፐርትና የፊክስድ አሴት ፎካል ፐርሰን ሆኖ እየሠራ ይገኛል፡፡
በወጣትነቱ ምርጥ እግር ኳስ ተጨዋች ነበር፡፡ (ከግብ ጠባቂነት እስከ ክንፍ ተጫዋችነት) በክለብ ደረጃ ለተንዳሆ በካፒቴንነት ተጫውቷል። አሰብ እያለ በራስ ገዙ ሠራተኛ ማኅበር የኢንዱስትሪ ግንኙነት ኃላፊ ሆኖ ሠርቷል። በተለያዩ የአስተዳደር ስፍራዎች ላይም አገልግሏል። በመንግሥት ለውጥ ጊዜ ወደ አገሩ የተመለሰው በእግር ጉዞ በጅቡቲ በኩል አድርጎ በከፊል በመኪና እና በባቡር በማቆራረጥ ነበር። ጅቡቲ ሪፐብሊክ በኤክስፖርት ሥራ ለሰባት ዓመታት ተመላልሶ ሠርቷል፡፡ ምዕራብ አፍሪካና መካከለኛ ምሥራቅ አገሮችም በአጭር ኮንትራክቶች የኤክስፖርት ሥራ ሠርቷል።
አገር መጎብኘት ስለሚወድ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ላይ በስፔሻል ቱር ጋይድነት ሠርቷል፡፡ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፥ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ተጉዟል። የመጀመሪያ ዲግሪውን በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ያገኘ ሲሆን፤ በጊዜው የመመረቂያ ጽሑፉን የሠራውም "የባሕር በር ፍለጋ" በሚል ርእስ ነበር። በድኅረ ዲግሪ አውዳዊ (ፐብሊክ) አስተዳደር ሲመረቅ ደግሞ ጥናታዊ ጽሑፉን የሠራው "ፍትሐዊ መንግሥትና ሀብት አጠቃቀም" ላይ ነበር። በአጠቃላይ አዲስ አበባ መቀመጫውን አድርጎ የተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ላይ እየተዘዋወረ ሠርቷል።
የሕይወት ጉዞው፥ ልምዱንና ዕውቀቱን አገናዝቦ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊና ምክረ ሐሳባዊ ጽሑፎቹን እንደ ቅዳሜ መዝናኛ ፕሮግራም (በ1970ዎቹ)፥ ዋልታ (በ1980ዎቹ መጨረሻ) ላይ የልብወለድ ሥራዎቹን አቅርቧል። በ2000 ዓ.ም መግቢያ በባለአደራ አስተዳደሩ ዘመን በርካታ ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ጽሑፎችን ጽፏል። በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ ጽፏል። በሐበሻ ወግ መጽሔት ላይ እምነት፥ ፖለቲካ፥ ሰብዓዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ (እንደየሁኔታው) በእውነተኛና በብዕር ስም በመጠቀም ወደ 190 የሚጠጉ ጽሑፎችን አስነብቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለጽሑፉ ክፍያን ጠይቆም ሆነ ተቀብሎ አያውቅም — ተመስገን ጌታሁን።
ፋልስ ለአንባቢያን ያደረሰው የመጀመሪያ መጽሐፉ ሲሆን በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ችግሮችና መፍትሔ ላይ ይዘቱን አድርጓል። ዕውቀቱና የሕይወት ክሂሎቱ፥ ጨዋታ አዋቂነቱ፥ አንደበተርዕትነቱ. . . ሳይቀሩ በብዕሩ በኩል ተንጸባርቀዋል።

Product Details

Synopses & Reviews

About the Author