About us
ያቤቶ በ ታህሳስ 2003 ዓም በ ደረጀ እና ፌይ በሚባሉ ጓደኛማቾች ተመሰረተ።ያቤቶ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የድረገጽ ገበያ ሲሆን ወደ በይነ መረቡ እንዲቀላቀል ምክንያት የሆነው የመስራቾቹ የኢትዮጵያ ምርቶችን ለማግኘት ካጋጠማቸው ችግር ተነስተው ነው። ይህ የሆነበትም ምክንያት ወቅቱ በአውሮፓና አሜሪካ የድህረገጽ ግብይት በተለይም አማዞንን ጨምሮ ሌሎችም ተዋናኞች በመስፋፋታቸው ምንም አይነት ምርት ማግኘት በጣም ቀላል ነበር። የሃገራችን ምርት ሲሆን ግን በተለይ ከአገር ውጭ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ውጭ ለሚኖረው ሰው በጣም አስፈላጊ የሆኑ በቀላሉ ያለ ብዙ ውጣ ወረድ ሊገኙ የሚገባቸው ለምሳሌ መጽሃፍት፣ሽሮ፣በርበሬ፣ያገር ባህል አልባሳትና ቁሳቁሶች፣የልጆች ማስተማሪያ ፊደሎች ለብዙ ሰው መሰርታዊ የሆኑ ነገሮች ናቸው። ነገር ግን በየትኛውም ድረገጽ ማግኘት አስቸጋሪ ነበር። በወቅቱ የነበረው እንዚህን ምርቶች ለማግኘት አንድም በቤተሰብ ማስላክ ካልሆነ በትንንሽ የሃበሻ ገበያዎች በመጠቀም ነበር። እሱም ለምግብ ነክ ነገሮች እንጂ ለሌላው በቂ አልነበረም።
ያቤቶ ጠንክሮ እንዲሰራ እስካሁን እንዲዘልቅ ያደረገውም ያለውን ችግር ለመፍታት የመጀመሪያውን ርምጃ መራመድ ወሳኘ እንደሆነ ሰለሚያምን ነው።
አሁን ምርቶች በተሻለ የሚገኙበት ብዙ አማራጮች ያሉበት ሰዓት ደርሰናል። አሁን የሃገር ውስጥ ፍላጎቱ በጣም ጨምሯል።ወቅቱ ይዞት የሚመጣውን ተግዳሮት መኖሩ ግልጽ ነው። ይህም ሆኖ ግን ገንዘቡን አውጥቶ ለመግዛት የሚፈልግን ደንበኛ ፍላጎት ማርካት መቻል ከምንም በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ብለን በጽኑ እናምናለን። ስራችን ይህ ነው!!!!
ደንበኞቻችን እናንተም ደንበኞቻችን በመግዛት ብቻ አይደለም ስህተታችንን ሳታልፉ ንገሩን!!!!
ለማንኛውም መልእክት ጻፉልን ደውሉልን
ስልክ:00251 911 361955
ኢሜል: info@yabeto.com