ጥቁር ሽታ

ጥቁር ሽታ

Regular price
$3.00
Sale price
$3.00
Regular price
$1.00
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

የማለዳዋ ጀንበር የሰደደችዉ ብርሃን ዘሃ በመስኮቶቹ በመግባት በመስታዎቶቹ መንፀባረቅ ይዟል ፡፡ ሰዉየዉ በመስኮት አሾሉኮ አይኖቹን ወደ ሰማይ ላከ፡፡ የድመት ፊት የምታክለዉን ፊቱን እንደስፖኪዮ ወደኔ ቀለነሰዉ፡፡
“ከሰማና ከፀሃይ በስፋት የሚተልቀዉ ማነዉ/” አለኝ ከመቅፅበት፡፡
“ሰማይ ነዋ !”
“ብርሃንን የምታጎናፅፈን ግን ትንሽዋ ፀሃይ ናት፡፡”
ገረመኝ፡፡
“ከዋክብት ኢምንቶች ናቸዉ አይደል/ ማታ ማታ ግን ግዙፉን ሰማይ የሚያስዉቡት ግን እነሱ ናቸዉ ፡፡
ከበጋ እና ከክረምት የሚረዝመዉ የቱ ነዉ /በጋ ነዉ ፡፡ ዘር እየተዘራበት ፣ እህል እየታጨደበት የፍጥረት እስትንፋስ እንዳይቆም ፣ ሕይወት እንድትቀጥል የሚያደርገዉ ግን ከበጋ የሚያንሰዉ ክረምት ነዉ ፡፡
ከጋን እና ከጠጠር ግን ጋን እንደሚተልቅ ግን ሁሉም ያዉቃል፡፡ ትልቁ ጋን እንዲቀመጥ የሚያስችለዉ ትንሹ ጠጠር መሆኑን ግን አብዛኛዉ ሰዉ አያገናዝብም ፡፡
ከምጣድ እና ከጉልቻ ምጣድ ይሰፋል ፤ ግና ያለ ጉልቻ ምጣድ ማለት ጥቅም የለሽ ተራ ሸክላ ይሆናል ፡፡
እየሰማኸኝ ነዉ አይደል / ደሞ ስማኝ ፤ ባትፈልግም አትስማኝ ፤ ግን ስማ ! ለኔ አይደለም ፤ ለራስህ ስትል ስማ!
ልብ “ሰዉ “በሚባል አገር ዉስጥ የወደቀች ብይ ናት ፡፡ ቺ ትንሽ ብይ አምፃ ቀጥ ባለች ቅፅበት ግን ትልቁ ሰዉ ከእዉነት ወደ አስክሬንነት ዜግነቱ ይቀየራል፡፡
ከቅፅበት እና ዘላለም የቱ የሚረዝም እንደሆነ ብጠይቅህ ዘለዓለም እንደሆነ አፍታ ሳትቆይ ትነግረኛለህ ፡፡ ዘለአለም የተፈጠረዉ ትንሽ እንኳ በማይገልፀዉ ትንሹ ቅፅበት ዉስጥ መሆኑን ግን አትነገረኝም፡፡ ልንገርህ / ዘለዓለም ዝርትርጥ ነዉ፡፡
የቅፅበጽ ጥበት ዉስጥ ነዉ ዉልደት ያለዉ ፤ የቅፅበት ጥበት ዉስጥ ነዉ ሞት ያለዉ፡፡
ዘመናት ከቀናት ቢረዝሙም ዘመናት እና ፍጥረታት በሞላ የተፈጠሩት በስድስት ቀናት ዉስጥ ብቻ ነዉ፡፡
አሁንም ልንገርህ! ትሪሊዮን ከአንድ በልጣል ፡፡ ከትሪሊዮን የሚበዙትን ፍጥረታት እና አለማት ጨምሮ ሰዉን ከነኮከቦቹ የፈጠረዉ ግን አንድ ነዉ ፡፡ አንድ ፈጣሪ!!፡፡
ወደ መፅሐፉ ተጎነበሰ፡፡
እንደተጎነበሰ…
“በብዙ ዉስጥ ትንሽ ከመኖር በትንሽ ዉስጥ ብዙ መኖር ይበልጣል
#ጥቁር ሽታ
መሀመድ ነስሩ

Product Details

Synopses & Reviews

About the Author

መሀመድ ነስሩ