ሕፃን እንደነበርኩ አማርኛ አስተማሪያችን "ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ?" ብለው ጠየቁኝ: "አላድግም አልኳቸው!!"፡፡
ንዝረቱ ሱዳን ድረስ በሚሰማ ኩርኩም አጋጩኝ፡፡ ገጭ !! በ'ሬክተር ስኬል' ምናምን ቁጥር የተመዘገበ ኩርኩም በሽመልስ ሀብቴ ትምህርት ቤት ሁለተኛ 'ዲ' ሰነፍ መደዳ ሶስተኛው ዴስክ ላይ...ጥቁር ሰሌዳው እያደገ እያደገ ሄዶ ግድግዳውን የሸፈነው እስኪመስለኝ ፊት ለፊቴ የሚታየኝ ነገር ሁሉ ጨለማ ሆነ፡፡የቀኔ ማብሪያና ማጥፊያ አናቴ ላይ ተገጥሞ በኩርኩም የሚበራና የሚጠፋ ዓይነት...'ገጭ' ሲል እልም!! ቀኑ ጨለመብኝ፡፡ ማክሰኞ ቀን ነበር...ማክሰኞ ጨለመ...!!
ይሄ ኩርኩም የሚገባው ለእማማ ዙርያሽ ነበር...(የሰው ሀቅ ነው የወሰድኩት )እሳቸው ናቸው የመስኮታቸውን መስታወት ለወፍ በወረወርኩት ድንጋይ የሰበርኩባቸው ቀን መንደሩ ሁሉ እየሰማ "ይሄ ያስታውቃል አያድግም"ያሉኝ፡፡ ደግም የባሕል መድሀኒት አዋቂ ናቸው፡፡ ትንቢት ቀመስ የሀኪም ትዕዛዝ ብናገር ይህን የሚያክል ኩርኩም...?
በኩርኩም የ'አታድግም!' ትንቢቱን አክሽፈውት ነው መሰል አደግኩ!! ፀረ ትንቢት ኩርኩም፡፡" ልጅህን በኩርኩም አጋጨው: ሲያድግ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ይመኛልና፡፡"
Product Details