ዮቶር ኮብላይ ካህን - yabeto

ዮቶር ኮብላይ ካህን

Regular price
$3.17
Sale price
$3.17
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

ብዙ ሰዎች የራሳቸውን ማንነት ከመረዳት ይልቅ የሌሎችን ማንነት በመጠየቅ በመመርመር ዕድሜያቸውን ያባክናሉ። እነዚህ ሰዎች የራሳቸውን የታሪክ አሻራ ትተው ከማለፍ ይልቅ ጥቂቶች ታሪካቸውን ሰርተው እንዲያልፍ መሰላል በመሆን ያገለግላሉ። ራሳቸው ሊፅፉ የሚችሉት ታሪክ አፍንጫቸው ስር፤ሌሎች ያንን ታሪክ እንዲፅፉት መረማመጃ መንገድ ይሆናሉ።
ሥልጣኔ ምንድን ነው?...የሰው ልጅ፣አስቀድሞ በነፍሱ ካልሰለጠነ ፣በሰውነቱ ካልሰለጠነ፣በማንነቱ ካልሰለጠነ ምኑን ነው ሰለጠነ የምንለው?...መገልገያ ቁስን ነው?...በእርግጥም የሰው ልጅ ቁሶች ከሰራቸው ከሰው ልጅ በላይ ሰልጥነዋል። ተራቀውማል። እነዚህ ቁሶችእንደ ሰው ልጅ ነፍስ ቢኖራቸው ኖሮ ከሰው ልጅ በላይ አስተዋዮች በሆኑ ነበር።
የሰው ልጅ ሁለት አይኖች እውነትን ሳይሆን ነፀብራቃዊ ምስሉን ይመለከተሉ። አስተዋይ ልቦና ግን በንስር ዓይን ይመሰላል። ከሰማይ አናት ላይ ሆኖ ውቅያኖስ ውስጥ ያለን እውነት መመልከት ይችላልና።
(በአለማየሁ ደመቀ)

Product Details

"እስቲ ይሄን ሥልጣኔ ያላችሁትን ነገር በጥሞና ተመልከቱት።
የዘመንኛው ቁሳዊ ሥልጣኔ ግኝቶችን ልብ በሏቸው።ዓለም ላለባት ችግር መፍትሄ ከመሻት ይልቅ፣ግኝቶቹ ራሳቸው ከምንም የከፋ ችግር እየሆኑ እንዲያውም የቀደሙትን ችግሮች እስከማስረሳት ደርሰዋል።ግኝቶቹ ከሚያስከትሉት ጠንቅ ይልቅ በግኝቶቹ የሚገኘው ኃይል ገንዘብና ዝና ይበልጥ ትኩረት ተሰቶታል።
በዚህ ሠለጠነ ባላችሁት ዘመን ሰላምን በምድር ላይ ለማራቀቅ የተደረገ ጥረት ሳይኖር ፤የጦር መሳሪያዎችን ይበልጥ አጥፊ አድርጎ ለማራቀቅ በየደቂቃው ብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ይወጣል።በዚህም ሳቢያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት በሦስት ዓመት ተኩል ዕድሜ ብቻ ሃያ ሚሊዮን ያህል ወታደሮችና ብዙ ሚሊዮን ሰላማዊ ሰወች ተጨፍጭፈዋል።ለሃያ ሁለት ዓመታት ያህል ይበልጥ ሲራቀቅ ቆየና ደግሞ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአምስት ዓመት እድሜ ውስጥ ከ50 ሚሊዮን በላይ ሰወችን አጨደ።ከዚያም ዘመን በኋላ የዓለም ጦርነት ተብሎ አይጠራ እንጂ በየሀገራቱ የተደረጉ ጦርነቶች ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰወችን አጭዷል።
"ታዲያ ሰው ያልሰለጠነበት ሥልጣኔ ምንድ ነው?.....
ሥልጣኔ መጀመር ያለበት ከነፍስ ነው።በመንፈስ ስትሰለጥን በማንነትህ ላይ ስልጣኔ ይኖርሃል። ስራህም መልካም፣ፍሬህም ፍቅርና ሰላም ይሆናል።በዚህ የዘመናዊው ሥልጣኔ ዘመን የረሃብና የቸነፈር ክንድ ይበልጥ በርትቷል። ለምን ቢባል ለአንድ የተፈጥሮ በሽታ መድኃኒት ለመፈለግ ከሚወጣው ገንዘብ ይልቅ ሌላ አዲስ በሽታ ለመፍጠር ይሄ ነው የማይባል ገንዘብ ይወጣልና ነው።
ብዙ ሚሊዮን የአለም ረሃብተኞች የረሃብን ስሙን እንኳን እንዳይሰሙ ለማድረግ ከጦር መሳሪያው ስልጣኔ ካዝና ላይ ጥቂት ገንዘብ መዝገኑ ብቻ በቂ ነበር።
"ለዚህ ነው የሰው ልጅ በመንፈስ ካልሰለጠነ በቀር ፍቅርና ሰላምን አያገኝም የምልህ። ለዚህ ነው ከእርካታ እልፍኝ ተጋብዛችሁ ሳለ ታዳሚዋ መሆን ሳትችሉ እንደተራባችሁ የምታልፉት።ኑሯችሁ ሊበጠስ አንድ ሀሙስ የቀረው ያህል ከሯል። በዚህ የኑሮ ግብግብ ውስጥ ላለመውደቅ ሳያሰልሱ መሮጥ ነውና ፤ቤተሰብ፤ጓደኛ፤ህብረተሰብ፤ሀገር መላው የሰው ዘር ሳይሉ በግለኝነት መገስገስ የዓለሙ ሁሉ ታሪክ ሆኗል። ታዲያ እርካታን የቱ ጋር ቆማችሁ ትረኩባት? ደስታን ከማን ጋር ሆናችሁ ታጣጥሟት?
የዘመናዊው ስልጣኔ ግብኃይልና ገንዘብ ነው።ኃይልን እና ገንዘብን ቅድሚያ ባደረገ ግስጋሴ ውስጥ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ ይነግሳል።ከመከባበር ይልቅ መናናቅ ይንሰራፋል።ከወዳጅነት ይልቅ ጠላትነት ይበረታል። መንፈሳዊው ስልጣኔ የተመሰረተው ፍቅር ላይ ነው። ፍቅር ደግሞ የሰብአዊነት ቁልፍ ነው።ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረበት ሰው ራሱን ለፍቅር ያስገዛል። በዘመናዊው ወይም በቁሳዊው ሥልጣኔ ውስጥ ያላቹ ተዋናይነት ያልገዛላቹ እርካታ እና ሰላም በመንፈስ ብትሰለጥኑ ኖሮ ሁሌም ከደጃፋችሁ ይኖራል። ወደ ውስጣችሁ ወደ መሰረታችሁ በመመለስ ለይ ትጉ። ትላንት በገነነው ላይ ዛሬ ሌላው ገንኖ የትላንቱን ገናና በሚያስረሳው ዓለም አትወናበዱ።
ዛሬ ተጨብጭቦለት ነገ በሌላው ጭብጨባ በሚዋጠው ወረተኛ አለም አትታለሉ።
"ይቺ ዓለም ምንም ውብና የምታጓጓ መስላ ብትታያችሁ ጥንት የነገስታትና የባለፀጎች መናኸሪያ የነበረችው ውቧ ባቢሎንም ከእነጌጧና ሥልጣኔዋ ጠፍታለች።" ............
#ዮቶር! ኮብላይ ካህን

Synopses & Reviews

"አይዞህ!... በጉዞህ በርታ ብቻ።እውነትን ይበልጥ እየተረዳህ በመጣህ ቁጥር ስቃይ ውስጥህ ይሞታል"ብላ ሹክ ስትለኝ ሰማኋት።ድምጿውስጥ የደስታዬ ሺህ እጥፍ የሆነ የደስታ ሲቃ ሲሰማኝ....
"እኔና አንቺ ምንና ምን ነን?"ብዬ ጠየኳት።
"እኔና አንተ እረኛና በግ ነን።እኔ ነፍስህ ፣እረኛህ ነኝ።አንተ ደግሞ የጠፋኸው በጌ ነህ። አሁን በሩቅ ላይህ ስለቻልኩ ነው እንዲህ የፈነደቅኩት። አንተስ አልታወቀህም?በሩቁ ልታየኝ ስለቻልክ እኮ ነው እንዲህ የፈነጠዝከው።አንተም ወደ እኔ ና።እኔም ወደአንተ እመጣለው።ልክ ስንገናኝ የጠፋህ በግ አትሆንም -እረኛ አለህና።ቀበሮም አያሰጋህም -እኔ እረኛህ ነቅቼ እጠብቅሀለውና። ግን በድጋሚ አትቅበዝበዝ -ላገኝህ ቀርቤያለሁና።"ብላ መለሰችልኝ።
"ፈጽሞ አልቅበዘበዝም። በመካከላችን ያለውን መሰናክል ሁሉ አልፌ እንድንገናኝ እበረታለው።"
ብዬ ቃል ገባሁላት።
ዓለማየሁ ደመቀ
ዮቶር ኮብላይ ካህን በተሰኘ መጽሐፍ ላይ ገጽ 21-22

About the Author