የትዳር ወግ

የትዳር ወግ

Regular price
$12.00
Sale price
$12.00
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

ለመሆኑ ትዳር ምንድር ነው ? ስኬታማ ትዳር የነበራቸው ሰዎችስ ተግዳሮቱን እንዴት አለፉት ? አሸናፊ ያደረጋቸው ምሥጥርስ ምንድር ነው ? የሚሉ ጥያቄዎችን ማሰላሰል ከጀመርኩም ሰነባብቻለሁ ::
የጨበጡትና በሩቁ የሚያውቁት ትዳር ለየቅል እየሆነባቸው ግራ የተጋቡ ሰዎችም ደጋግመው ያጋጥሙኛል ::
.... ሦስቱ ጉልቻ እንደ እሳት ዓምድ የሚያስፈራቸው ሰዎችስ ቁጥራቸው ስንት ይሆን ?
እነዚህን ውስብስብ ጥያቄዎች እያውጠነጠንኩ በነበርኩበት ከሦስት ዓመት በፊት አንድ በጋብቻ ዙሪያ የተጠና ጥናት ተመለከትኩ ::
በአሜሪካ ሀገር ከሚጋቡ ጥንዶች መካከል እኩሌታው የሚሆኑት ፍቺ ፈጽመዋል :: ' ዕድላችንን እንሞክር ' ብለው ለሁለተኛ ጊዜ ወደትዳር ከገቡት መካከልም 60 በመቶ ዕጣቸው መፋትት ሆኗል :: ከትዳር በፊት በደባልነት የሚኖሩ ጥንዶች ቁጥራቸው በየጊዜው እየጨመረ ሲሆን እነዚሁ ጥንዶች ከተጋቡ በኋላ የመፋታት ዕድላቸውም ሰፊ ሆኖ ታይቷል :: እንዲያውም ከሦስት ልጆች አንዱ እንዲህ ባለው ደባልነት ኑሮ የሚወለዱ ናቸው :: በተጨማሪም እንዲህ ባለ ሰባራ ትዳር ያደጉ ልጆችም የመለያየት ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው ::
እኔም ስለትዳር የሚወጡ መረጃዎች ለምን እንዲህ አስደንጋጭ ሆኑ ?! በእኛ ሀገር ያለው ሁኔታስ በቁጥር ባይሰፈርም የችግሩ አሳሳቢነት ምን ያህል ይሆን ? የትዳር ፈተናስ ቀድሞውንም ይህን ያህል የበረታ ነበር ወይንስ ከዘመኑ ጋር እየጠነከረ መጣ ?! ለመሆኑ ይህ ትዳር የሚባል ነገር ምንድር ነው ?!ስኬታማ ትዳርን ለመምራት የተቻላቸው ሰዎችስ የአሸናፊነት ምስጥራቸው ምንድን ነው ?! "
የተነሱት አምስቱ ጉዳዮች ብዙ ቁም ነገሮችን ይዘዋል:: የትዳርን እውነተኛ ትርጉም መረዳት መቻል ቁልፍ ጉዳይ የመሆኑን ያህል፤ ፍቅርን ፍለጋ የምንጓዝበትን ጎዳና በደንብ ማወቁም ለስኬታማ ትዳር አስተዋጾው ከፍ ያለ መሆኑን እንዲሁም ፍቅር እንዳያረጅ ማድረጉ ምርጫው በእጃች እንደሆነ በደንብ መረዳት ችያለሁ:: በተመሳሳይ ፍቅርና ጠብ የማይነጣጠሉ ጉዳዮች መሆናቸውን አውቆ ጠብን በዕርቅ እያሸነፉ ፍቅርን ዘላቂ ማድረግ እንደሚቻል እንዲሁም ትዳር ፍጻሜው እንዲያምር ከሁሉም ወገን ብርቱ ጥረት እንደሚፈልግም አሳይቶኛል:: የትዳርን ውጣ ውረድ ከትውውቅ እስከ ፍጻሜው ቁልጭ አድርጎ ማሳዬት መቻሉም ሥራውን ተወዳጅ ያደርገዋል:: ከሰው ተሞክሮ ከስኬቱም ከውድቀቱም እንደመማር የመሰለ ምን የተሻለ አጋጣሚስ ይኖራል? ወድቀው ከተነሱት፤ ፈተናውን በድል ከተሻገሩት ባለትዳሮች ለመማር “የትዳር ወግ” ይመቻል:: ደግሞም እንደ እኛ ባለ ሽፍንፍኑ በበዛበት ሀገር እንዲህ ችግሮች እርቃናቸው ሲወጣ የትዳር ጣጣው፤ ውጣ ውረዱ የገጠማቸው ሰዎች ለካ ህመሙ የእኔ ጎጆ ጋር ብቻ አይደለም ያለው በሚል መጽናናት፤ መበርታት ያስችላቸዋል::
ጸሐፊው ከዚህ ቀደም " ቅን መሪ " እና " ባለራዕይ መሪ " የተሰኙ እጅግ ተወዳጅ መጻሕፍትን አስነብቧል ::