የቀይ ኮከብ ጥሪ - yabeto

የቀይ ኮከብ ጥሪ

Regular price
$1.94
Sale price
$1.94
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

"...የህልውናችን ማእከልም ሆድ ነው። ሰው ሲናደድ አንጀቱ ደበነ ወይም ሆዱ አረረ፤ ሲያዝን ወይም ሲጨነቅ፥አንጀቱን በላው፥ አንጀቱ ተላወሰ፥ ሆዱን ባር ባር አለው፥ ከውሳኔ ሲደርስ፥ አንጀቱ ቆረጠ፤ ትእግስት ሲያሳይ - ሆደ ሰፊ ነው፤ ማሺንክ ሲሆን ሆዱ አይገኝም፤ ሲወድ ካንጀቱ ይወዳል፤ ሲጠላም እንደዚሁ፤ አንዱ ሌላውን ማሞኘት ሳይችል፥ ሆድ ለ ሆድ ይተዋወቃሉ፤ ብቻ ምናለፋችሁ ስናስብም፥ ስንወድም፥ ስንጠላም፥ ስናዝንም፥ ቂም ስንይዝም፥ ብልጥ ስንሆንም፥ ሁሉም በሆዳችን ነው!...
ተረቶቻችን ከሆድ አይርቁም። ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል። እስቲ ጨምሩበት። ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው።.... ተናደሀል መሰለኝ! ይህ ተረት በምን ትዝ አለህ ጃል? አለው። ምነው አልናደድ? ተው ቻለው ሆዴ እያልኩ ነው። የሰው ሆድ ከውቅያኖስ ይሰፋል ይሉ የለ? ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም አለው አይዞህ። አለው።
...በሆዳችን ስለምናስብ እኮ ነው ጭንቅላታችን የማይሰራው። ነገራችሁ አንጀቴን እያራሰው ነው። አለ ጌታቸው። አንጀት ይቆርጣል በል እንጂ! አለ ጠበቃው።... ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ አሉ።
...ጎመን በጤና ብዬ ዘጋሁት በየቀኑ ከምወነጀል። ሆድና ጀርባ አታድርገኝ። የኢትዮጲያ ሆድ ጅንጉርጉር ነው።....."
የቀይ ኮከብ ጥሪ ከበዓሉ ግርማ ገፅ 251-252
እኔ ኢትዮጵያዊያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ። በጭንብል ተሸፍነን የምንኖር ሕዝቦች ነን። ለሰው የምናሳየው ገጽታ እና እውነተኛው ባሕርያችን የተለያዩ ናቸው። እንደ ተረታችን፣ ሥነ-ጽሑፋችን እና ንግግራችን ባሕርያችንም ሰምና ወርቅ ነው። በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት መለኪያ የለንም፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን የግል ጥቅማችን ነው። ለዚህም ነው ተንኮል የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው።
ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው መርህ አንድ ብቻ ነው፤ የግል ጥቅም። ከራስ በላይ ነፋስ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል፤ ሰውን ማመን ቀብሮ፥ ይሉታል ከነተረቱ። የሚያሳዝን ነው። ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን። ስንዋሽ ህሊናችንን ቅንጣት ታህል አይቆረቁረንም። እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል። ተንኮል ምቀኝነትና ቅናት ባህላችን ነው።" ገጽ 217።

Product Details

Synopses & Reviews

About the Author