የመሀል ልጅ - yabeto

የመሀል ልጅ

Regular price
$2.96
Sale price
$2.96
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

.......ህይወት ትክ ብለህ ስታያት የምታስፈራ ናት፤ በሾኬ እና በጠረባ የተሞላች መሰናክሏ ብዙ...ዳገትና ቁልቁለቷ መዓት።
ትክ ብሎ ላላያት አስመሳይነቷን ላልተረዳ ፤ማነኝ ምንድነኝ? ብሎ ዋጋውን ላልጠየቀ ፤ሆዱን ስትሞላለት ተመስገን ለሚልላት ምቹ ናት ።ጎርባጣው ጎረበጠኝ ካላልክ እኮ የሚመች ነገር አታስብም ።ካላሰብክ ደሞ ጎርባጣው ላይ ዝንትአለም ትተኛለህ፤ አይቆረቁርህም። የህይወት ሚስጥራ የመኖር ጥጉ ፤ክፋት ማንአለብኝነት ምን አገባኝ እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ከሆነ ምንድነው የሰብዓዊነት ትርጉም? ካንተ ሃይማኖት ያልሆነን ሰው መውደድ ካልቻልክ ካንተ ዘር ያልሆነን ሰው ማክበር ካልቻልክ ለእኔ ልብ የሌለህ እና አእምሮ የሌለህ ቀፎ ነህ ! ከሁሉ በፊት ሰብዓዊነት ይቀድማል! ከዛ ቀጥሎ ስለ ሀገር ስለ ታሪክ ሃይማኖት ታወራለኛለህ .......እውነት ግን የቱ ነው የሚበልጠው?
ኛ ሰው <ጦስህን ይዞት ይሂድ> የሚያውቀው ብርጭቆ ስትሰብር ብቻ ነው አንተ ስትወድቅ ግን <ብዬ ነበር> ይላል እንጂ ማንም እጁን ሰዶ ሊያነሳህ አይጥርም አይዞህ እኔም አልፌበታለሁ ማለት ክብሩን መሳት ይሆንበታል ። ደግመህ እንደማትንሰራራ እርግጠኛ ነው። ምፅ ብሎ በቁምህ ይቀብርሃል። ከትቢያ አራግፈህ ለመነሳት ትንፈራፈራለህ ምፅ ይሉልሀል ምፅ እናቱ ሞታ እኮ ነው ምፅ በጣም አንባቢ ስለነበር እኮ ነው ምፅ ካይሆኑ ሠው ጋር ገጥሞ እኮ ነው እያሉ በምፅ ሲፈራረቁብህ ፈሪ ትሆናለህ። የሚቀጥለውን እርምጃህን መቼም አታምነውም ወደኋላ ስታይ ግዜህ ይነጉዳል። በዚህ ሁሉ መሀል ህይወት እንደ ክፉ አስተማሪ መቅጣቷን አታቆምም። አይምሮህ ከገደብ በላይ ይሆንበታል ትደክማለህ በቃ ሰው ነሃ!!

Product Details

Synopses & Reviews

ሴቶቻችን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የስነ-ፅሁፉ መድረክ ላይ በአጫጭር ልቦለዶች እየሾሩበት ይገኛሉ። ሜሪ ፈለቀ - በጠበኛ እውነቶች ፤ ትእግስት ታፈረ - በባሲልቆስ እንባ በአስደናቂ ስነ-ፀሁፋዊ ብቃት ራሳቸውን የገለጡ ወጣት ደራሲዎች ሲሆኑ - የመሀል ልጅ - ደራሲዋ ወጣት ቤዛዊት ብርሀኑ በራሷ መልክ "እነሆ በረከት" ብለናለች።
"This is the only real concern of the artist, to recreate out of the disorder of life that order which is art" ይላል ታላቁ James Baldwin።
እውነት ነው ደራሲም የስነ-ፅሁፍ አርቲስት ነውና የህይወትን ምስቅልቅል በስርአት ሰትሮ፤ የተመሳቀለውን እንደየመልኩ ወግ አስይዞ ከነፍሱ ጥበብን በብእሩ ይወልዳል። ቤዛዊትም ስምንት ራሳቸውን የቻሉ በአንድ ገመድም የሚተሳሰሩ ስምንትም አንድም የሆኑ ምስቅልቆችን በየመልካቸው ቀንብባ የመሀል ልጅን ተገላግላለች።
~ © መግቢያ ~
የመሀል ልጅ እንደሌሎቹ መፅሀፍት መግቢያ የለውም። ቀጥታ ወደመሀሉ ያመራል። ስለምን መንደርደርያ አልተበጀለትም? ምናልባት "የመሀል ልጅ መነሻ የሌለው መተላለፊያ " ስለሆነ ይሆናል። መሀል በመጀመሪያና በመጨረሻ መካከል ላይ የሚገኝ ነውና ፀሀፊዋ የመፅሀፋን ርእስ ላይ ተመርኩዛ ካለምንም መንደርደሪያ ወደ መተላለፊያው ያመራችን ይመስለኛል።
~ © ታሪክ 1 : ህልሜ ~
"May you fall asleep in the arms of a dream,
so beautifully,
you'll wake up crying" - - - Michael Faudet
ማነው ትዝታ ውስጥ ህልሙን የፈለገ? ህልሙን ልጅነቱ ውስጥ የቀበረስ ማነው? ቅዠቱ ህልሙ የሆነበትስ? ከሞት ጋር ታግሎ "ህይወትን በህይወት የቀየረ" ጀግና አባት ያለው ማነው? ይህ ታሪክ ከልጅነት፣ ህልምና ትዝታ ሰበዞች ተሰፍቶ በትናንት ላይ ይዋልላል።
~© ታሪክ 2 : ሀምሌ ገገማ ነው ~
"There is water in my eyes
and fire in my heart
do you want a drink?
or a spark?" - - - Al Shareef Al-Radhly
ለምንድነው የነፍሶቻችን የዘላለም ቁስል የሚመጣው የኔ ከምንላቸው ከነፍስያችን ሰዎች የሚሆነው? የፍቅር ሀውልት በልባችን የተከሉ ሰዎች ለምንድን ነው እንደጦር የሳሉ የልብ ፍላፃዎችን ሰንቅረውብን ለመሄድ የሚጣደፉት? የመጨረሻውን የደስታ ከፍታ ያስጨበጡን ሰዎች የነፍስ ውጋት ጫፉንም አሳቅፈውን የሚሄዱት ለምንድን ነው? እንደ አክሱም ያገዘፉን ለምንድነው እንደ ብርጭቆ ፈጥፍጠውን ልባችን ላይ የእሾህ አክሊል ደፍተው ከህይወታችን ጓዳ በኩራት ተንጠራርተው ተወጣጥረው የሚሾልኩት?
ሀምሌ ገገማ ነው የአንድ ባል ታሪክ አይደለም። ይልቁንስ በታሪኩ ውስጥ በአባታዊዉ ማህበረሰብ ተኮትኩቶ የጎመራ ሀበሻዊ ወንድነትን (ከወንድነትም ባልነትን) ፣ ወንድነቱ ውስጥ የተደመሰሰው ሰው የመሆን እሴት፣ የወንድነቱን ውሀ ልክ የሻረ ሴትነት እጣፈንታ (ከሴትነትም ሚስትነት) ፣ በነፍስ ሙታ በስጋዋ ህልው የሆነች ሴትነት መልክዓ ነፍስ ወ ስጋ በውብ ቋንቋና የሀሳብ ፍሰት ተተርከውበታል።
ሚስትነትና እናትነት ምንና ምን ናቸው? በሚስትነት ውስጥ ያለ እናትነትን ገፍቶ በሚስትነት ውስጥ ያለን ውበት ብቻ የሚያሳድ ባል ሰውነቱ የት ላይ ነው? ለምንድነው ባልነት እኛ ሀገር ውስጥ ሰው መሆን የሚጎለው? ማህበረሰባዊ የልክነት ሚዛኖቻችን በእርግጥ ልክ ናቸውን? ልኩ ልክ ካልሆነ ስለምን በልክነት ሚዛን እንሰፈርበታለን? እስከመቼ ነው በዚህ "የልክነት ሚዛን" መመዘን የሚቀጥለው? የልክነት መስፈሪያው ሚዛን ልክነቱን የሚነቀንቀው የተሻለ የልክነት ሚዛን ለመቀበል ልቡ ስለምን ደነገነ? ስለምን ነፍሱ እንደ ሀምሌ ገገመ??? .... ብዙ ብዙ የሞራል ጥያቄዎች ይፈለፈሉበታል ከሀምሌ ገገማ ውስጥ። ለኔ ይሄ ታሪክ የመፅሀፋ epic ነው።
~ © ታሪክ 3: ነገረ ሎሚ ~
ስድስት አረንጎዴዎች : በላይ (እንቁ አረንጓዴ) ፣ ከበደ (ጥቁር አረንጓዴ) ፣ አፀደ (ቅጠልያ አረንጓዴ) ፣ ኤልያስ (አረንጓዴ) እና ወይኒ (ሻምሮክ አረንጓዴ) አምስቱ አረንጓዴዎች እየተፈራረቁ አፀዱን (ኒዮን አረንጓዴ) ሲያፈኩትና ሲያጠውልጉት ይታያል። አፀዱ Symbolic ነው። ከወርቃማው አረንጓዴ አፀድ ውጭ ያሉ አምስቱ አረንጓዴዎች መልክዓ ሰው ናቸው፤ መርዛም ተናካሽ ሴሰኛና ሴረኛ ነፍሶች ፤ የዋህ አፍቃሪ ሆደ ሰፊ ብፅእት ነፍሶች። የነፍሶች ጦርነት!
~ © ታሪክ 4 : ሰው ብቻ ~
"You need a chaos in your soul to give birth to a dancing star." - - - Nietzsche
መቼቱ ድሬ ነው። ታይዋን ሰፈርና ገንደ ቆሬ ያመላልሰናል። ድህነት እንደ ሳማ ሲፋጅ ፣ እንደ በርበሬ ሲለባለብ ፣ ድህነት ሆድ የሚሉት የማይሞላ ስልቻን እያገላበጠ የሰው ልጅን ሲጋልብ ታይዋለህ። ድህነት ግን ለምንድነው ነፍስን ቆስቁሶ የጥበብ መደወሪያ የሚሆነው?
ነኢማ የታሪኩ ማሳለጫ ሁናለች። ነኢማ ማለት ጉዱ ካሳ ማለት ናት ቀኝ ስትሏት ግራ የምትል። ነኢማ deviant ናት ሲሻት አላህን 'የምትሳፈጥ' ሲላት የማህበረሰቡን ባህሉና ወጉን አለኝ የሚለው ደግነቱንና ሀይማኖተኛ ነኝ ባይነቱን ገላልባ - አንተ ነኝ የምትለውን ነህ ወይ ? - ብላ ነን የምንለውን እንድመረምር የምታስችለን የህሊናችን ኮምፓስ ናት፤ ልብ ብለን ካስተዋልናት አላህ አንተ ራሱ ነህ የምትባለውን ነህን ? የምትል ትመስላለች ነኢማ ድህነት ስጋዋ ላይ የተሞሸረ የአላህ ፍጡር።
በታሪኩ ውስጥ በድህነት ላይ የሚዋኝ ሴትነት ለጭን መደጎሻነት ሲፈተን ይታያል። ድህነትና ቅንዝር "ይዋጣልን!!" ሲባባሉ ይታያሉ። የነኢማን እናት ስንመለከት ድህነት ጋር ፍልሚያ የሚገጥመው ቅንዝር ግራ አጋቢ ነው። ከተፈጥሮ ከመነጨ ጥልቅ የወሲብ መሻት የተፀነሰ ቅንዝረኝነት? ወይንስ የሆድ ጥያቄ ብቻውን አምጦ የወለደው ቅንዝር? ወይንስ ሁለቱም አንድ ላይ ተዳብለው? ድህነትና ወሲብ ግን ማነው አንድ ላይ የገመዳቸው? የነኢማን ድህነት ማነው የፃፈው- እድሏ? እርሷ? ቤተሰቧ? ማህበረሰቡ? አላህ? ድህነት አዝለነው ሁሌም እሹሩሩ የምንለው እንቆቅልሽ ያደረገብን ማነው???
~ © ታሪክ 5 : የመሀል ልጅ ~
ይሄ ደራሲዋ ለመፅሀፉ ርእስነት የመረጠችው ታሪክን የያዘ ነው። የመሀሉ ልጅ ማነው? በባድመ ጦርነት ሊዋጋ ሂዶ ከንፈሩን ጥይት የሸረፈው ወንዱ (ወንድሻ) ማነው? ሚራ ማናት? አሩራስ? ይሄን ክፍል አንባቢው እራሱ ያጣጥመው።
~© ታሪክ 6 : ፋና ~
ይሄ ታሪክ ደራሲ አሌክስ አብርሀም ዶክተር አሸብር እና ሎሎችም በሚለው ውብ መፅሀፉ - ከሰሀራ በታች - በሚል ርእስ የተረከው ንጥል ታሪክ ቀጣይ ታሪክ ነው። ፍናን አስታወሳችኋት? ፋና ማለት የኮሜርሱ ተማሪ የአብርሽ የፍቅር ሀውልት የነበረችው ፣ የፍቅርተ እህት ፣ የእማማ አመለወርቅ ውድ ልጅ ፣ አብርሽ " ፋና እኮ ርስት ናት ከፀሀይ መውጫ እስከ ፀሀይ መግቢያ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ የተዘረጋች" ያለላት ፋና በቤዛዊት ብእር ነፍስ ዘርታ ተገልጣለች።
~ © ታሪክ 7 : ክሽ ክሽ ~
ምንጭ ከጃፋር ሽፋ

About the Author

ቤዛዊት ዘሪሁን