ዛምራ

ዛምራ

Regular price
$3.00
Sale price
$3.00
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

ዛምራ
234 ገጾች አሉት። በሦስተኛ መደብ አጻጻፍ የተጻፈ ድርሰት ነው። መጽሐፉ ሙሉ ለሙሉ ልቦለድ ነው ብዬ መቀበል አልፈልግም ምክንያቱም ብዙ ሃቆች አሉት። መቼቱ ከደርግ ዘመነ መንግስት ጀምሮ አሁን ያለውን መንግሥት ይነካል። ከጎጃም አንስቶ ሩስያ፣ ከሩስያ ግብጽ፣ ከግብጽ አዲስ አበባ ከአዲስ አበባ ይወጣና በደብረ ብርሃን ወስዶን ሙሉ ወሎን አስጎብኝቶን ጎንደር ደርሶ በባህርዳር ተመልሶ አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ላይ መቼቱ ያርጋል።
በ1969 የዚያድባሬ መንግሥት ኢትዮጵያን ወረረ ... በዚህ ሁኔታ የቆሎ ተማሪዎች ታፍሰው ተወስደው ወደ ወታደር ቤት ገቡ። እነዚህ የታፈሱት የቄስ ተማሪዎች በቂ የውትድርና ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ወደ እስራኤል ተልከው በሞሳድ ውስጥ ስልጠና ተሶጥቷቸው የኢትዮጵያ ሰላይ ይሆናሉ። በሃገራቸው እና በተለያዩ የአለማችን ክፍል ተሰራጭተው ለኢትዮጵያ መሰለል ይጀምራሉ። ደራሲው የብዙዎችን የቆሎ ተማሪዎች (ሰላዮች) ህይወት ወደ ጎን ትቶ ታሪኩን ሊነግሩለት የሚችሉትን የጥቂት ሰላዮች ህይወት ይዞ ድርሰቱን ይቀጥላል። እነዚህ የኢትዮጵያ ሰላዮች በሄዱበት ሃገር በስለላ ሃገራቸውን እያገለገሉ ጎን ለጎን ደግሞ ዘመናዊት ትምህርት እየተማሩ ህይወታቸውን ይገፋሉ።
ዋና ገጸባህሪው ደግሞ የስለላ እውቀቱ እንዲጨምር ተብሎ ለትምህርት ከኢትዮጵያ ወደ ሩስያ ሃገር ይላካል። የደርግ መንግሥት ረቢን የኬሚስትሪ እውቀት ታግዞ የአቶሚክ ቅመማ ለማካሄድ ነበር በወቅቱ ወደ ሩስያ የላከው። ነገር ግን ረቢን በሩስያ እየተማረ እያለ የደርግ መንግሥት ሰለወደቀ በተማረበት በሞስኮ ዩንቨርስቲ መምህር ሆኖ መስራት በዛው ቀረ። በሚያስተምርበት ዩንቨርስቲ ውስጥ የፊዚክስ ተማሪ ሆነ። ... የቴክኖሎጂ ሳይንስ ካጠና በኋላ በሞስኮ ዩንቨርስቲ ውስጥ የኒውክለር ኢንጅነር ሆነ። በጥቂት አመታት ውስጥ የፕሮፌሰር ማእረግ አገኘ ...
(... አሁን ሩስያ ውስጥ ከእርሱ የበለጠ በኬሚስትሪ እውቀት የተካነ ጠቢብ የለም - እየተባለ ይነገራል። የመጀመሪያውን የፔሬዲክ ቴብል ካረቀቀው ከማንዴሊቭ ቀጥሎ የሚጠራው ረቢ ነው። በሩስያ ውስጥ ከእርሱ ዕውቀት ያልቀሰመ ተማሪ የለም እየተባለ ይወራል። አንዳንዴም፣ ከኬሚስትሪ እውቀቱ ጀርባ በፊዝክሱም ብዙ መጽሐፍትን ከማገላበጡም በላይ በፊዚክሱም የተራቀቀ ነው እየተባለም ይጠራል። በኒውክለር ኢንጅነሪንግም ስለተራቀቀበት በዛ ውስጥም ቁልፍ ሰው እርሱ እንደሆነ ብዙዎቹ የሩስያ ሊቃውንት ይስማማሉ።

Product Details

Synopses & Reviews