እውነት + እምነትና ሕይወት - yabeto

እውነት + እምነትና ሕይወት

Regular price
$4.22
Sale price
$4.22
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

እውነት:- ምንነቱ እና አደጋው
ጠያቄ: የምትነግረን ነገር በሙሉ እውነት ሆኖ ሳለ ስለምን ብዙኃን ይቃወሙሃል?
ትክክለኛ ምክንያት- የምናገረው እውነት መሆኑ ነው።
እውነት አደገኛ ናት። በተለይ ሐሰተኛ የሆነ ተምኔታዊ ሕይወታቸውን በተዋቡ ሐሰቶች እና አስደሳች በሆኑ ሐሳባዊ ሕልሞች በመኖር ላይ ለሚገኙ በሙሉ እውነት በርግጥም አደገኛ ናት።
እነዚህና መሰል ሰዎች እውነትን በጠላትነት ይመከቷታል።
ምክንያታቸው ደግሞ ዕድሜያቸውን በሙሉ ያመኑበትን የኖሩበትን ሐሰተኛ አመለካከቶች ስለሚያፈርስባቸው ነው።
#እውነት ማለት የሐሰቶች ሁሉ ሞት ናት። በተዋቡ ቃላት የተናገሩትን ሀሰቶች ጨምሮ የምትገድል ናት።
ብዙኃን ለምን ነበር ሶቅራጠስ ላይ የተነሡበት? ሃይማኖተኞችስ ስለምን ነበር ኢየሱስን የተቃወሙት? የሁለቱም ጥፋት የብዙኃኑን እንቅልፍ እና ያማረ ሕልም መረበሻቸው ነበር።
ማንም ቢሆን ከምቹ እንቅልፍ መቀስቀስን አይወድም።
ብዙኃኑ ደግሞ ከእንቅልፋቸው በቀር ምንም የላቸውም። በሁሉም ስፍራ ለብዙኃኑ ሕልም በመሸጥ የከበሩ የሕልም ነጋዴዎች አሉ። ነጋዴዎቹ ሕዝብን ይበዘብዛሉ እንጂ በምላሹ ምንም አይሰጡትም።
ሁሉም ሃይማኖቶች የሰውን ልጅ ደካማ ጉን በመጠቀም ሕልም የሚሸጡ በዝባዦች ናቸው። እርግጥ የሰው ልጅ የማይገዳደረው ድክመት አለ ይኸውም ሞት ነው። ሁሉም ሰው ይሞታል። የሞትን እውነት ማንም ሊሸሸገው አይችልም።
ሁሉም ከተሞች የመቃብር ስፍራ ከከተማ ውጭ ያደርጋል። ሆኖም ግን ቦቻቸው መሆን ያለበት ከተሞች መሐል ነበር። መሐል ከተማ ቢሆኑ ለሁሉም ተመልካች የሞትን እውነተኛነት ደጋግመው ያስታውሱት ነበር።
በሕይወታችሁ ከሚከሰቱ ነገሮች መካከል ሞት ብቻ አይቀሬ ነው። ሞት ብቻ ገሃድ ነው። የትም ብትሄዱ ከሞት አታመልጡም።
ኦሾ/osho

Product Details

Synopses & Reviews

About the Author