አለመኖር - yabeto

አለመኖር

Regular price
$2.53
Sale price
$2.53
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

Product Details

በእናት ሆድ ውስጥ ጥጋብ ነው፤ ረሀብ የለም፡፡ በእናት ሆድ ውስጥ ሙቀት ነው፤ ብርድ የለም፡፡ ከሁሉም በላይ ግን በእናት ሆድ ውስጥ ጣዕር የለም፡፡ መስራትም የለም፡፡ በምቾት መንፈላሰስ እና በለስላሳ ውሀ ውስጥ መንሳፈፍ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ድሎት በተወለድንበት ቅፅበት ይለወጣል፡፡ መተንፈስ ግድ ይላል፡፡ ረሀብን ለማስታገስ መጥባት እንጀምራለን፡፡ ይበርደናል፤ ሙቀት ለማግኘት ከሌላው እንጠጋለን፡፡ ለመኖር፡፡ አለበለዚያ መኖር የለም፡፡ መታፈን፣ በረሀብ አለንጋ መቆላትና በብርድ ቆርፍዶ መሞት የፍርሀታችን ሁሉ መነሻ ይሆናሉ፡፡ በእናታችን ማህፀን የምናውቀው መኖርን ብቻነው፡፡ መወለድ አለመኖርን አመላካች ነው፡፡

"....አዎን መሸነፍ ነው። ፍቅር መሸነፍ ነው። ፍቅር መያዝ ነው። ፍቅር ለስሜት ተገዥ መሆን ማለት ነው። ፍቅር ከምክንያት ውጭ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው። ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጭ መሆን ነው።
ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው። ያስፈራል ፍቅር። የማይታከሙት ህመም ፤ የማይጠገን ቁስል ፤ የማያባራ እንባና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል።
የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን፤ ማፍቀር እራሱ ነው። ካፈቀርሽ በኋላ "እኔ" የምትይው ሁሉ ይጠፋል። ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ። በፈቃድሽ ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጭው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።
ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፤ እጅ መስጠት፤ ወዶ መግባት፤ ከራስ መነጠል ፤ መጥፋት ፤ በማያውቁት ሰው ውስጥ ገብቶ መሰደድ። አያስፈራም አትበይ ያስፈራል"

Synopses & Reviews

About the Author