ህይወት ግዛቷ ሲጣስ

ህይወት ግዛቷ ሲጣስ

Regular price
$3.00
Sale price
$3.00
Regular price
$1.00
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

ማሳለፍ እንደ ሞት ነው፣

አንድም ሰው አይቀረው፤

ሕይወት ፣ ሞት እና ራስን ማጥፋት

ራስን ማጥፋት የሠው ልጅ ከተፈጠረ ጀምሮ በሚባል መልኩ የቆየ እና የከረመ የኑሮው አንዱ መገለጫ ተደርጎ የሚቆጠር ጥንታዊ ድርጊት እንደሆነ፣ የታሪክ መዛግብት ይመሠክራሉ:: ራስን ማጥፋት በትርጓሜ ደረጃ ለመረዳት ያህል ከተረጎምነው አንድ ሠው የራሱን ሕይወት ሲያጠፋ ነው ማለት እንችላለን:: ይህ ትርጓሜ ግን ውስብስብ ከሆነው ራስን የማጥፋት ዝንባሌ እና ድርጊት አናጻር ካየነው ብዙም ገዢ ላይሆን ይችላል::

የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ንጉሡ አጥናፉ በግል፣ ማኅበረሰባዊ በሆነ ዕይታቸው እና ገጠመኞቻቸው ተነስተው ይህን መጽሐፍ ሊጽፉ እንደተነሱ የመጽሐፉ መግቢያ ላይ ይነግሩናል:: በዋነኝነትም ሠዎች ራሳቸውን ለምን እንደሚያጠፉ ከማየታችን በፊት ያ የሚጠፋው ሕይወት ምንድን ነው? ብለው ያጠይቃሉ:: (ገጽ 15)

ጥያቄው በራሱ ከባድ እና ውስብስብ መሆኑን የሚነግሩን ደራሲው፣ የበለጠ ጥያቄውን የሚያወሳስበው ደግሞ ሠዎች ይህን ጥያቄ ብዙ ግዜ የሚጠይቁት በሚጨነቁበት ወይም እሴቶቻቸው በሚጣሱበት የሕይወት አጋጣሚ ላይ በመሆኑ ነው:: የፍልስፍና ተማሪ እና ተመራማሪ ያልሆኑ ሠዎች እምብዛም እንዲህ ዓይነቱን ጥያቄ በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው አለመጠየቃቸውን ያስተውሏል ይሉናል ደራሲው::

“ሕይወት እንደ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ነው:: ጥቂቶች ሜዳሊያ ለማግኘት ጡንቻቸውን የሚያጠነክሩበት፤ ሌሎች ለታዳሚው የተለያዩ ነገሮችን በመሸጥ ትርፍ የሚያገኙበት እና ብዙዎች ደግሞ እንዴት እንደሚከናወን ለማየት የሚመጡበት ነው:: ”

ፓይታጎረስ

የሕይወትን ትርጉም ለመረዳት፤ ትርጉምን ራሱ መረዳት አለብን የሚሉን ደራሲው ሄደን- ሄደን ህይወትን መተርጎም ላይ እንቸገራለን ይሉናል:: ይህ ደግሞ የሚሆነው በተለያየ ምክንያት ነው፤ አንደኛው ስለ አንድ ነገር ትርጉም (ምልክት፣ ቃል) ስንሰጥ፤ ያ ትርጓሜ ከራሱ አልፎ ወደ ሌላ ነገር ማመልከቱ ነው:: በዚህ ሃሳብ ከተስማማን ትርጉሙን እንደ አመላካች የመውሰድ ችግር ላይ እንወድቃለንና ጉዳዩን የመተርጎም አቅም አይኖረንም ወይም ያንሰናል::

ሠዎች ስለ ሕይወት ትርጉም ሲጠየቁ በአዕምሮአቸው ውስጥ ከነሱ ሕይወት ውጭ ወደ ሆነ ነገር ያመለክታሉ:: ይህም ጥያቄውን ከመመለስ ወደ ፊት ማስተላለፍ ላይ መውደቅን ያስከትላል፤ እንዲህ ካሉት በሕይወት ትርጓሜ ዙሪያ ከሚሰጡ ትርጓሜዎች ወይም መረዳቶች አራቱን ያህል መጥቀስ ተገቢ ነው ብለው ደራሲው እነዚህን ይጠቅሳሉ :-

  • ልጆች
  • እግዚአብሔር
  • ከሕይወት በኋላ ያለው ሕይወትና
  • ሕይወት ትርጉም የለውም ብለው የሚደመድሙ ናችው

ይህ ማመልከት እንዳለ ሆኖ ለአንዳንዶች፡-

ሕይወት ጀብድ ነው

ሕይወት ተልዕኮ ነው

ሕይወት ታሪክ ነው

ሕይወት ጥበብ ነው

ሕይወት ፍላጎት ነው ወዘተ… (ገጽ 23)

ሕይወት ለሁላችን እያመለከተን እንዲሁም በራሱ ከነ ገደቡ እየተረጎምነው ስንሄድ ከላይ የጠቀስናቸውን ይመስላሉ እንደ ደራሲው አረዳድ::

ሞትስ ምንድን ነው?

ሕይወት ለሠው ልጅ ያለፈባቸው ነገሮች እንደሆኑና መጨረሻውም ቅርብ ይሁን እሩቅ በእርግጠኝነት ወደ ፍጻሜው እየተጠጋ መሆኑን የሚገነዘብበት ነው:: በዚህም ባለበት መቆም ወይም ወደ ኋላ መመለስ አለመቻሉና ወደ ፊት አንድ መዳረሻ ብቻ ሊኖረው የሚችል መሆኑን እሱም የራሱ የመኖር ሕልውና ማብቂያ እንደሆነ ይረዳል :: (ገጽ 24) ማብቂያው ነው ሞት እንደማለት::

ሠዎች ለምን ራሳቸውን ያጠፋሉ?

ጥፋት፣ ጥላቻና ጸብ

ሠዎች እንግዳ ለሆኑ ሠዎች የሚሠማቸው ያልተደበቀ ጥላቻ አብዛኛውን ግዜ በወዳጆች መካከል ሳይቀር እንኳ የሚቀሰቅሰው የጥላቻ ድርጊት፣ ለጥላቻ ዝግጁ መሆን፤ ሁሉም ምንጫቸው የማይታወቅ ነው:: እንዲህ ዓይነት ድርጊቶችን ለመግለጽ የሚገፋፋ ባህሪ ጸብ ጫሪነት ነው:: (ገጽ 32) በተፈጠሮአችን ያሉ ዝንባሌዎቻችን ናቸው እንደማለት::

ተስፋ መቁረጥ

እንደ ሠው፣ ከተስፋ መቁረጥ የበለጠ በአንድ ላይ የሚያስተሳስረንና ለሁላችንም በአብላጫው የጋራ የሆነ ገጠመኝ የለም ማለት ይቻላል:: ተስፋ መቁረጥ ሳይነገር፣ ሳይጠበቅና ሳንዘጋጅ የሚደርስ በመሆኑ በኛ ላይ ሲከሰት ሁሉም ነገር ከኛ ወጥቶ የሄደ ያህል ይሰማናል:: ጉልበታችንን በቀስታ ይዞ የሚሄድ፣ እኛነታችንን በአንድ ላይ የያዘውን መንፈስ ቀስ በቀስ ሊያወጣ ወይም ሊያባርር የሚችል ነው:: በየትኛውም መንገድ ተስፋ የቆረጠ ሠው ወደፊት ጉዞ ለመቀጠል አዳጋች ይሆንበታል:: ደግሞም፣ በሕይወት ውስጥ ከምናሸንፍባቸው ይበልጥ የምንሸነፍባቸው ይበዛሉና ይህንን የማያገናዝቡ ሕይወታቸውን ለመራራነትና ለተስፋ መቁረጥ ብሎም ለባሰ ሁኔታ ይጋብዟታል:: (ገጽ 35)

ሠዎች ከላይ በጥቂቱ ደራሲው በጠቀሷቸውና እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶችና አጋጣሚዎች ራሳቸውን ያጠፋሉ:: ሌላው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተነሱ ቁምነገሮች መጠቀስ ያለበት ራስን ለማጥፋት እንደ አንዱ ምክንያት የሚቆጠረው ሳናስብ የምናደርጋቸው ድርጊቶች ናቸው የሚለው ሥነ ልቡናዊ (Psychoanalysis) አስተሳሰብ ነው::

የተከለከሉና በማኅበረሰቡ የተወገዙ ግፊቶች በተደጋጋሚ ከ‹‹አንኮንሸስ›› ወደ ‹‹ኮንሸስ›› ለማለፍ በሚተጉ ጊዜ በራስ ያለ ዐመለካከት (ኤጎ) ይመልሳቸዋል:: ይህ ድርጊት ግጭቶችን ይፈጥራል:: ከዚያ ከከፋ ውጤቱ የአዕምሮ መቃወስን (neurosis) ያስከትላል:: የዚህ መጽሐፍ ጭብጥም ይህን ሃሳብ መግለጽ እንደሆነ ደራሲው ገጽ 45 ላይ አስቀምጠዋል::

ምን ጠላት መጣና በለሊት ጠራው፣

ለመሬት እንደሆን ቀድሞም የጁ ነው፤

በዚህ መጽሐፍ ደራሲ እምብዛም ትኩረት ያላገኘውን (በጥናትም፣ በሣይንስም፣ በሃይማኖትም) ርዕሠ-ጉዳይ አንስተው አከራካሪ፣ አሳሳቢ፣ ዐይን ገላጭ፣ ሸንቋጭ እና ታዛቢ ሃሳቦችን አነስተው ይሟገታሉ:: ራስን የማጥፋት ውስጣዊ ምክንያት (ለመግደል መፈለግ፣ ለመገደል መፈለግ እንዲሁም ለመሞት መፈለግ) እና ውጫዊ ምክንያት (የማኅበረሰብ አመለካከት፣ የቤተሰብ ሁኔታዎች፣ የአካባቢው ወግና ልማድ እና ያልተሟላ ስብዕና ዕድገት የሚያመጣው የመዛባት ሁኔታ) ብሎም ራስን ለማጥፋ የሚያበቁ ድንገተኛ ሁኔታዎችን፣ አዝማሚያ እና ዝንባሌዎችን ባጠቃላይ ራስን ስለማጥፋት በጥናት የተዳሰሱ ሃሳቦችን እና የግል ምልከታቸውን ከተለያዩ ገጠመኞቻቸው ጋር በአገራዊ ግጥም እያዋዙ ከባዱን እና የማይስበውን ርዕሠ-ጉዳይ ተነባቢ ለማድረግ ጥረት አድርገዋል::

ምናኔ (በዝግታ ራስን መግደል)፣ ሰማዕትነት (በምክንያት /ከፍ ላለ ሃሳብ/ መሞት)፣ የአልኮል ሱሰኛነት (በዝግታ የመሞት አዝማሚያ)፣ የራስን ዐካል ማስወገድ (ራስን የመጉዳት ዝንባሌ እና ራስን ወደ ማጥፋት ሊያደርስ የሚችል ጠቋሚ ምልክት)፣ ጦርነት (ሠዎች በፍቃድ ወደ ሞት የሚሄዱበት በምክንያት የተደገፈ ወይም ያልተደገፈ ምርጫ መውሰድ) እንዲሁም መሠልና ከራስ ማጥፋት ጋር ተያያዥ የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮችን አንስተው አጠር አጠር ያሉ ማብራራያ እና ትንታኔዎችን በዚህ መጽሐፋቸው ሠጥተዋል::

ማጠቃለያ

ሞት ይቅር ይላሉ ሞት ቢቀር አልወድም፣

                ድንጋዩም ዐፈሩም ከሠው ፊት አይከብድም፤

ራስን ለማጥፋት ቢያንስ ውጫዊ እና ውስጣዊ ምክንያቶች እንዳሉ ለመረዳት ይቻላል:: ጉዳዩም ውስብስብ እና ብዙዎቻችን ሠዎች ራሳቸውን ካጠፉ በኋላ፣ በተለመደ መልኩ የምንደርስባቸው ድምዳሜዎች ከእውነታው እጅግ የራቁ እና ጉዳዩን እንዳንረዳ ሲያደርጉን እንደዘለቁ ደራሲው ያምናሉ:: እናም፣ በሠከነ መንገድ ይህ ጉዳይ ውይይት እና ምርምር እንዲደረግበት ይጋብዛሉ፡፡ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል:: ተደጋግሞ የታየው ራስን የማጥፋት ጉዳይ የግለሰቡ ጉዳይ ተደርጎ ተትቷል፡፡ ይህ ግን፣ መቅረት እንዳለበት እና ማኅበራዊ እንዲሁም ሳይንሳዊ ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ አጽንዖት ሠጥተዋል:: (ገጽ 99)

እንደሚባለው ነው፤ ሁሉንም የራስ ማጥፋት ዝንባሌ እና ድርጊት ከሠው ልጅ ሕይወት ማጥፋት ባይቻልም እንኳ፣ በዳበረ ውይይት እና በተጠናከረ ጥናት እንዲሁም በሠው ልጅ ቁርጠኝነት አደጋውን መቀነስ ይቻላል:: የአንድንም ሠው የሕይወቱን ግዛት ከመጣስ ማዳን ከተቻለ እንደ ትልቅ ቁምነገር ይቆጠራል ብለው ያምናሉ- ደራሲው ንጉሡ አጥናፉ::

የህይወት ግዛቷ ደግሞ በተፈጥሮአዊ መንገድ እንደተሠመረላት ሁሉ ቢቻል በተፈጥሮአዊ መንገድ ካልሆነ ደግሞ ያለ ራስ ጣልቃ ገብነት ቢጣስ ምርጫቸው እንደሆነ ያስቀመጡ ይመስለኛል ደራሲው:: ያው ይመስለኛል ነው እንግዲህ::

Product Details

Synopses & Reviews

የሁፌን አቅጣጫ ሳይሆን የሁፌን theme የወሰድኩት በተጠቀሰው አርዕስት የታተመ ጥናታዊ መጽሐፍ አግኝቼ ነው፡፡ መጣጥፌን ከመጽሐፉ በአርዕስት ለማስተሳሰር ፈለኩ፡፡ ..ህይወት ግዛቷ ሲጣስ.. በሚል በዚሁ ዓመት ታትሞ ገበያ ላይ የዋለውን የንጉሱ አጥናፉን መሐፍ ስያሜ ተዋስኩ፡፡ . . . ስነምግባር፣ ግብረገብ፣ የማህበረሰብ ህግ፣ የሀይማኖት ህግ፣ የህሊና ህግ . . . እነዚህ ሁሉ ..ኤቲክስ.. በሚለው የፍልስፍና ዘርፍ ስር የሚጠኑ ንሰ ሀሳቦች ናቸው፡፡

. . . ስለ ..ኤቲክስ.. ወይንም ..ሞራል.. ለማውራት አይደለም ቀደም ባለው አረፍተ ነገሬ  . . . በተለይ ደግሞ ራሴን ጠያቂ እንጂ አጠያያቂ (አቧራ አድራጊ) አድርጌ ተመልክቼው አላውቅም፡፡ አላውቅም፤ ለማወቅ ግን እፈልጋለሁ፡፡
የስነ ምግባር እና የማህበረሰብ ህግን አለማወቄ የሞራል ጥያቄን ከመጠየቅ አያግደኝም፡፡ ከጥያቄዎች ግን ስመርጥ መጠንቀቅ አለብኝ፡፡ ምራጭ እና ምርጥ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ምራጭ እና ምርጡን የሚለውን የሚለየው የ..ዋጋ.. ጉዳይ ነው፡፡ ዋጋ የሌለው ጥያቄ ዋጋ ያለው መልስ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ዋጋው ያልተተመነ ጥያቄ ግን አጉልቶ መተመን . . . የመልሱንም ዋጋ ውድ ማድረግ ነው፡፡ ጥያቄውን በመፍራት እንዳላዩ ወይንም ጥያቄው እንደሌለ ማስመሰል ግን አይኔን እስከጨፈንኩ የእውነታ ግጭት እኔን አይነካኝም እንደማለት ነው፡፡ አይንን ገልጦ ግጭቱን ከተቻለ ማስወገድ ካልተቻለ አውቆ መቀበል ይሻላል፡፡
. . . እና መነሻዬ ..ዋጋ.. የምትለው ቃል ናት፡፡ አንድ ግለሰብ ትልቁን ዋጋ የሚሰጠው ለምንድን ነገር ነው? . . አንድ ማህበረሰብስ? . . . የግለሰብ እና የማህበረሰብ ዋጋ ምርጫዎችን የሚያቆራኝ ነጥብ አለ? Is an Individual an autonomous sub-whole, . . . Is the whole the sum of its Parts, or are the parts the sum of the whole? . . .
ነጠላው (Individual) ጥቅሉ ማህበረሰብ ላይ ተእኖ ሊያሳድር ይችላል? ወይንስ ማህበረሰቡ ግለሰቡ ላይ? . . . በአንድ ሰው ችግር ወይንም ስቃይ ማህበረሰብ ሊቸገር ወይንም ሊሰቃይ ይችላል ወይንስ ተገላቢጦሽ ነው? . . . አንድ ግለሰብ ህልውናውን ቢያጣ (ቢሞት) ማህበረሰብ ህልውናውን ያጣል? . . . ህሊና የግለሰብ ንብረት ናት የማህበረሰብ?
በተጨባጩ ህይወታችን ላይ ከሆነ መሰረታዊው ዋጋ በህልውና መገኘት ነው፡፡ ቀዳሚው ዋጋ እሱው ነው፡፡ እምነትም ሆነ እውቀት፣ እድገትም ሆነ ማንነት ከዚህ በመከተል የሚመጡ ናቸው፡፡
በግለሰብ እና ማህበረሰብ ላይ ያሉ ትስስሮችን ጠንካራነት ለመመስከር፤ እንደዚሁም፤ በተቃራኒው ለማፍረስ ከሚወሰዱ እርምጃዎች አንደኛው የራስን ህይወት በራስ እጅ ማጥፋት ነው፡፡ . . . ግለሰብ ራሱን በራሱ እጅ ማጥፋት ግብረገባዊ (Moral) ነው ወይንስ ኢሞራላዊ? የሚለው ነው የዛሬ ሁፌ መሰረታዊ ጥያቄ፤ . . . ጥያቄውን በተለያየ መረጃ መገንባት እና መጠየቅ ያለበት መሆኑን ማሳየት እንጂ መልስ ማግኘት ተልዕኮዬ አይደለም፡፡ መልሱም ቀላል አይመስለኝም፡፡
አልታዘዝም ባይነት (ግዛት ጣሽነት)
አለመታዘዝ ወይንም ትዕዛዝ ተላላፊነት በክርስቲያኖች ዘንድ እንደ ትልቁ ኃጢአት ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ አለመታዘዝን በቃሉ ተራ እና ከፍተኛ ትርጉም ለሁለት ከፍለን የተመለከትነው እንደሆነ ማለቴ ነው፡፡ በቃሉ ከፍተኛ ትርጉም አልታዘዝም ባይነቱ ዋናውን ዋጋ (በህልውና መገኘት) አልቀበልም ብሎ የምርጫ እርምጃ ሲወስድ ነው፡፡
lምሳሌ:- በጆን ሚልተን |Paradise Lost.. ኤፒክ ግ_M:- መልአክ ዋና ስራው እና  ተፈጥሮው ከላከው ተነስቶ ወደ ተላከበት ተልዕኮውን ማድረስ እና መመለስ ነበር፡፡ ብርሀን አምጪ ተደርጐ የተሰራው ሊቀ መልአክ ብርሀን አላመጣም ካለ፤ የተፈጠረበትን ትርጉም ተፃረረ ማለት ነው፡፡ ዋናውን የህልውናውን ዋጋ አልቀበልም ካለበት ጊዜ ጀምሮ መልአክ ተብሎ ሊጠራ አይችልም፡፡
በዚሁ አተያይ ሰውም ዋነኛ ..ዋጋው.. በህልውና መገኘት ስለሆነ፤ በራሱ ፈቃድ  በህልውና መገኘቱን ማቆም ከፈለገ፤ አልታዘዝም ባይነት ውስጥ ገብቷል፡፡ ለዋናው ዋጋ መታዘዝ ህይወት ከሆነ ትዕዛዝ እንቢተኝነቱ ደግሞ ሞት ነው፡፡ የራስን ህልውና በራስ እጅ እና ፈቃድ መሻር፡፡ የህይወትን ግዛት (ትዕዛዝ) መጣስ!
ዋናውን አለመታዘዝ ከሌሎች ተራ ትዕዛዝ እንቢታዎች የሚለያቸው፤ ተራዎቹ በህልውና ክልል ውስጥ በህይወት በመኖር ሂደት እንቢ የምንላቸው በመሆናቸው ላይ ነው፡፡ ዋናው አለመታዘዝ ግን (Suicide) አንዴ ከተመረጠ መመለስ አይችልም፡፡ አንዴ ከተመረጠ ከዛ የሚቀጥል ምርጫ ዳግም እስከ መጨረሻው አይኖርም፡፡ ለግለሰብ የምርጫ መጨረሻ ራስን ማጥፋት ነው፡፡
የምርጫ መጨረሻ ሂደቶች  
የራስ ህይውና ላይ አለመታዘዝ (Suicide) ደረጃ ከመደረሱ በፊት የተለያዩ አማራጮች እንደ ማምለጫ ይሞከራሉ፡፡ ሞት የመጨረሻው አማራጭ የሚሆነው፤ ፈላጊው መውጫ ሲያጣ ነው፡፡ ከአማራጭ ፍለጋ እስከ ሞት ውሳኔ ድረስ ያሉትን ሂደቶች ማርሻል ስሊናርድ በአራት ደረጃ እንደሚከተለው ከፍሎ ÃSqMÈcêL፡፡  
1. ረጅም ዘመን በችግር የተሞላ ህይወት 2. በድሮው ላይ በቅርቡ የተጨመረ ሌላ የችግር መከሰት እና የድሮውን እና አዲሱን በአንድ ላይ ለመፍታት የሚደረግ መፍጨርጨር 3. በልምድ የሚገኝ ችግርን በተለምዶ የመፍታት ክህሎት ማጠር፤ ወይንም፤ የነበረውን ክህሎት በተስፋ መቁረጥ ምክንያት ማጣት 4. የተስፋ ሙሉ ለሙሉ ሞት
ራስን ማጥፋት እና መስዋዕትነት  
በተለያዩ የሀይማኖት እሳቤዎች ወይንም የእምነት አይነቶች ራስን ማጥፋት ለራስ ችግር ማምለጫነት ወይንም ከስቃይ መገላገያነት ሲውል የተወገዘ ቢሆንም፤ ራስን ማጥፋቱ በሀይማኖት ምክንያት ሲውል ግን የተደገፈ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ግለሰቡ ለራሱ ሲል የወሰደው የዋጋ ምርጫ ያስወግዘዋል፤ ለማህበረሰቡ ዋጋ ሲል የወሰደው ምርጫ በራሱ ህልውና ላይ ግን ሲሆን መስዋእትነት ተብሎ ይጠራል፡፡ ተራው (ሲያስኮንን)፤ ለብዙሀኑ በሚል አላማ የተደረገው ግን በሰማይ (ለሀይማኖተኞቹ) ድቅን በምድር ደግሞ የጀግና ማዕረግን ያጐናፋል፡፡ (a |dying in the Lord.. is a death which is no death at all (Rev. 14:15)  
እርግጥ፤ በክርስቲያንም ሆነ በሌሎች የእምነት መሐፍት ራስን ማጥፋት በግል ሀጢአት ሆኖ የተቀመጠበት ቦታ የለም፡፡ የምድር ህይወት በስቃይ እና በፀፀት የተሞላ ስለሆነ የስጋን ሸክም መቻል ያቃተው፤ ሸክሙን በራሱ ፍቃድ አውርዶ ቢጥልም፤ እንደ መለኮታዊ ወንጀል ተደርጐ በመሐፍቱ አይጠቀስም፡፡ በ452 A.D በአርሊስ የተሰበሰበው ጉባኤ የራስን ህይወት ማጥፋት ወንጀል መሆኑን በይፋ አውጆ አፀደቀ፡፡ ድርጊቱን የሚፈሙት ደግሞ እርኩስ መንፈስ የተጠናወታቸው መሆኑ ተሰመረበት፡፡ በዚህ ረገድ የሞቱትም bቤtKRStEÃnùM ቅር እንዳይቀበሩ ፍትሀትም እንዳይሰጣቸው በሚል ተደንግጐ ዘለቀ፡፡ ይህ የካ.ቤ ህግ የተነሣው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፡፡ . . . ነገር ግን የተገለፀው ውግዘት ለሀይማኖቱ ወይንም ለእምነቱ በተፈሙ መስዋእትነቶች ላይ ተግባራዊ አይሆንም ነበር፡፡
|It’s only If the action is undertaken exclusively and consciously out of consideration for one’s own person that self killing becomes self-murder...  
የመስዋእትነትን መንፈስ ለመገንዘብ ከክርስቶስ ስቅላት በላይ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን የለም፡፡ የክርስቶስ ፈተና፣ መከራ፣ እና ስቅላት የራሱን ህይወት ብቻ ትኩረት ያደረገ ሳይሆን፤ የሰው ልጆችን ሀጢአት ለመሻር፣ ከራሱ በላይ ብዙሀኑን ምክንያት በማድረግ ነበር፡፡ . . . ነገር ግን እዚህ ላይ ክርስቶስም ሞቱን አስቀድሞ ስለተነበየ ህይወቱን በፍቃዱ (ለገዳዮቹም ቢሆን) አሳልፎ መስጠቱ (እንደ አምላክ እና ሰውነቱ) በሰውኛ ከተተረጐመ ህይወት በራስ እጅ እንደ ማጥፋት ይቆጠርበታል፡፡ መስዋእትነትም የ Suicide አይነት ወይንም ዘርፍ ነው፡፡
ከክርስቶስ ዘመን በፊት በኦሪት ህግ የህዝቡን ሀጢአት በላያቸው ላይ እንዲሸከሙ የሚደረጉት የመስዋዕት በጐች ነበሩ፡፡ በጐቹ በቁጥር ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው በግ ወይ ፍየል የህዝቡን ሀጢአት በካህኑ አማካኝነት ተጭኖበት ወደ ጫካ ይለቀቃል፡፡ ሁለተኛው በእሳት ተቃጥሎ ጭሱ ወደ ሰማይ ይሄዳል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ሁለቱም ፍየሎች የመስዋዕት አይነት ናቸው፡፡ |Scapegoat.. የሚለው ቃል ከዚህ የመጣ እንደሆነ ይታሰባል፡፡ የህዝቡን ኃጢአት ተሸክሞ ወደ ጫካ የተለቀቀውን ፍየል ይወክላል፡፡ የቃሉ ፍቺ ..መስዋእት.. ማለት ቢሆንም፤ ቀጥተኛ ትርጉሙ ግን ..ያመለጠው ፍየል.. እንደማለት ነው፡፡ ወይንም የሌላውን እዳ የከፈለው ሰለባ. . .፡፡
መስዋእትነት ለፈጣሪ ክብር ወይንም ግዛት ሲባል ብቻ ሳይሆን፤ ለሀገር ክብር እና ምድራዊ ግዛት ክብር ሲባል የተከናወነ ሊሆን ይችላል፡፡ ሲሆንም ታይቷል፡፡ አፄ ቴዎድሮስ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ግን የአፄ ቴዎድሮስ ሽጉጥ በራሳቸው ላይ የጮኸው ሀገሩን ነፃ ለማውጣት ተብሎ ሳይሆን፤ ራሳቸውን ከውርደት ነፃ ለማውጣት የተከናወነ ይመስላል፡፡ የእሳቸው ሞት በሰአቱ ለሀገራቸው ምንም የሚጐዳውም የሚጠቅመውም ነገር አልነበረም፡፡ ጥቅሙም ሆነ ጉዳቱ፣ ቁጭቱም ሆነ እፎይታው . . . ለራሳቸው ካልጠቀማቸው በቀር . . .፡፡  
ሳምሶን (የደሊላ) ወይንም የኦሪቱ፤ በጠላቶቹ እጅ ወድቆ (በሴት ተሸንፎ በነበረበት ጊዜ፤ ወደ ጠላቶቹ መዝናኛነት እንዲቀየር ፍልስጤማዊያኑ ፍቃዳቸው ሆነ፡፡ ድላቸውን ለመጋራት ለፌሽታ በተሰበሰቡበት አዳራሽ ሳምሶን የወሰደው እርምጃ የራሱን ነብስ ማጥፋትን እና የጠላትን ህይወት ማጥፋትን የቀላቀለ፤ መለያያውን መስመር ያደበዘዘ ድርጊት ነበር፡፡ ሳምሶን የቤቱን ምሰሶ በጉልበት ስቦ ሲያፈርስ፤ በጠላቶቹ እጅ ያለውን የራሱን ህይወት ማሳጠር ብቻ አልነበረም አላማው፡፡ ጠላቶቹን ከራሱ ጋር ደባልቆ መፍጀት እንጂ፡፡ ..ሳይቀድሙኝ ልቅደም እና እኔም ልከተል . . ... የመሰለ እርምጃ ወሰደ ሳምሶን የኦሪቱ፡፡ የራሱን ተስፋ ያጣ (አይኑ የጠፋ) ህልውና አሸናፊ (ሟች)  ለማድረግ አስቦ ተሳካለት፡፡ ጠላቶቹ፤ የፈጣሪ ጠላት ስለሆኑ መስዋእትነቱ እንደ ፈጣሪ ግዛት ጽድቅ እንደተቆጠረለት ይታመናል፡፡ (ወይንስ ከጠላቶቹ ሴት (ደሊላ) ጋር በማመንዘሩ ጽድቁ እና ሀጢአቱ እርስ በራሱ ተጣጣ?)
ራስን ማጥፋት በፈላስፋዎች እይታ
ራስን ማጥፋት በፈላስፎች ዘንድ በሁለት ንፍ እንጂ በመሀል ሰፋሪ (moderate position) የማይቀመጥ ነገር ነው፡፡ አንደኛው ጐራ ራስን ማጥፋት ዋናው የነፃነት እና የአብዮተኛነት መገለጫ እንደሆነ አድርጐ የሚደግፍ ነው፡፡ እስቶይኮች (Stoicism) የዚህ አንድ ጽንፍ ጥሩ ምሳሌ ለሆን ይችላል፡፡ ለሾፐን ሀወርም ራስን ማጥፋት እንደ ከፍተኛው አመ እና ነፃነት መቀዳጃ አድርጐ ነው የሚቆጥረው፡፡ የሁለተኛው ጐራ ደግሞ፤ ራስን ማጥፋት በምንም መልኩ ወይንም ለምንም አይነት ጥሩ ግብ ማስፈፀሚያነትም ቢሆን መደገፍ የሌለበት ነው የሚሉ ናቸው፡፡ አማኑኤል ካንት እና የካንት የፊሎሶፊ ጽንሰ ሀሳብ አራማጆች (Kantians)  በዚሁ ሁለተኛ ጐራ ሊመደቡ የሚችሉ ናቸው፡፡
ሶቅራጥስ ሰውን እንደ ፈጣሪ ንብረት አድርጐ በመቁጠሩ ራስን ማጥፋት የአምላክን (አማልክትን) ንብረት ሳያስፈቅዱ እንደማጥፋት ስለሚሆን ቁጣን (wrath) ያስከትላል ባይ ነው፤ ወይንም ነበር (እንደ ፕሌቶ ዘገባ)፡፡ ነገር ግን፤ የአማልክቶቹ በንብረታቸው ላይ ውድመት እንዲከሰት መፍቀዳቸውን ወይንም ፍጡሩ [NBrtÜ (ሰው)] ራሱን ማጥፋት እንደተፈቀደለት የሚያሳዩበት መግለጫ ይሰጣሉም ይላል፡፡ ይኼንን መፍቀዳቸውን የሚገልፁት፡- ራስን ከማጥፋት ውጭ ምንም አማራጭ የሌለው ሁኔታ በፍጡሩ ህይወት መንገድ ላይ በመደንቀር ነው ይለናል፤ ፕሌቶ (the permission of the gods could be made manifest by a “visible nessity of dying” as had been imposed on Socrates himself. ይሄም የአማልክቶቹ ራስን የማጥፋት ፈቃድ በፍጡሩ ላይ ተሰጥቶ በራሱ በሶቅራጥስ ህይወት ላይ ይታያል፤ በማለት ፕሌቶ የሶቅራጥስን የአሟሟት ሂደት ለሀሳቡ መደገፊያነት እንደ ማረጋገጫ ያቀርባል፡፡  
ሶቅራጥስ በተከሰሰበት ወንጀል በህዝብ ምርጫ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ወደ ዘብጥያ በወረደ ጊዜ፤ ከእስር ቤት የማምለጫ እድል ቀርቦለት እንቢ ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡ በህዝብ (State) የተፈረደበት የሞት ፍርድ፤ ወደ ራስን ማጥፋት (Suicide) የሚለውጠው፡- ከሞት የማምለጥ አማራጭ እንዳለ እያወቀ ሞትን በመምረጡ፤ ቅጣቱን የህግ ፍርድ ሳይሆን ራስን ማጥፋት በራስ ምርጫ ለመሞት መፈለግ መሆኑን YmsKRb¬L፡፡ ያደርግበታል፡፡ የተከሰሰበት (ወጣቱን የማበላሸት) አጀንዳ ትክክል እንዳልሆነ ሲከራከር የቆየ ሰው ክርክሩ በድምጽ ብልጫ ቢረታም፤ እውነቱ ተረታ ማለት አልነበረም፡፡
ስለዚህ፤ በተከፈተለት አማራጭ ቢያመልጥም ለእውነቱ ሲል እንጂ ህዝቡን እና የሀገሩን ህግ በመፍራት እንዳልሆነ ግልጽ ነበር፡፡ ለሀገሩ ህግ የተሳሳተ ፍርድ ተገዝቶ አሜን ሲል ህይወትን በሞት ተክቷል፡፡ ከመኖር ይበልጥም መሞትን በራሱ ፈቃድ መርጧል፡፡ ይህንን ምርጫውን ነው ፕሌቶ “visible necessity of dying” ብሎ የሚጠራው፡፡ እዚህ ላይ የአማልክቱን ንብረት (ራሱ ሶቅራጥስ) ለማጥፋት በቂ ፈቃድ መቀበሉ እርግጥ ነው ወይንስ አይደለም? የሚለው ጥያቄ አሻሚ መልስ ሳይኖረው የሚቀር አይመስልም፡፡
ዋናው ነጥብ
ዋናው ነጥብ ላይ ከመድረሳችን በፊት ከዋናው ነጥብ ጋር የተያያዙ ብዙ ሌሎች ንዑስ ነጥቦች አሉ፡፡ The whole is the sum of the parts ..ጥቅሉ የተናጠል ክፍል ወይንም ክፍልፋዮች ድምር ነው.. የሚል የተለመደ አባባል አለ፡፡ አሁን ግን በዚህ አባባል የማመኛው ወቅት ያለፈበት ይመስላል፡፡ ጥቅሉ የክፍልፋይ ክፍሎቹ ድምር ቢሆንም ድምሩ ከጥቅሉ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ተናጠሎቹ ያላቸው የተነጣጠለ ማንነት፣ ተመን፣ ሀይል ይበልጥ ተደምረው ሲጠቃለሉ የበለጠ ማንነት፣ ተመን፣ ሀይል ሊሰጡ ወይንም ፈጥረው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ክፍልፋዮቹን እንደ ግለሰብ ጥቅሉን እንደ ማህበረሰቡ ማየት እንችላለን፡፡ ወይም ራስን መግደል የግለሰብ ጣጣ ወይንም እዳ ከሚሆንበት መጠን በላይ ድምር ውጤቱ የማኅበረሰብ እዳ እና ጣጣ መሆኑ ያመዝናል፡፡ የግለቡ ህልውናን ማጣት ከማኅበረሰቡ ህልውና ማጣት ጋር እኩል ብቻ ሳይሆን የበለጠ ነው፡፡ ግብረገብ የራሱ ልዕለ ህግ (Universal law) አለው? ወይንስ በማህበረሰብ የሚወሰን እንጂ ጠቅላይ ማስማሚያ የሌለው ጽንሰ ሀሳብ ነው የሚለው አከራካሪ ጥያቄ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት፤ የራስን ህይወት በራስ ፍቃድ እና እጅ መውሰድም እንደ ማህበረሰቡ እምነት፣ አስተሳሰብ፣ ህገደንብ የሚለዋወጥና ድርጊቱ ከጀግንነት እስከ ወንጀል፤ ከጽድቅ እስከ ኩነኔ ተደርጐ የሚታሰብ ሆኗል፤ እስካሁንም እንደዛው እየታሰበ ነው፡፡
ራስን ማጥፋት የሞራል ዝቅጠት ቢሆንም ዝቅጠቱ የተመዘነው በግለሰቡ ህሊና ነው ወይንስ በማኅበረሰቡ የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም፡፡ ማኅበረሰቡ እና ግለሰቡ በሚያደርጉት ግንኙነት ማኅበረሰቡ በጥቅሉ ብዙ ግለሰቦችን ስላቀፈ ህሊና ያለው ይመስላል እንጂ ህሊና በመሠረቱ የግለሰብ ነው፡፡ በዚህ የግለሰብ ህሊና እና በማኅበረሰብ ግዑዝ ህሊና (ደንብ፣ ስነ ሥርዓት፣ ባህል፣ ኃይማኖት፣ ነውር፣ ውግዘት፣ ውርደት፣ መገለል. . . ወዘተ) መሃል በሚከሰት ተራክቦ ግለሰቡ የዋጠ እና መናኛ ይመስላል፡፡ የመናኛነቱ ስሜት ለሚከሰት የስነ ልቦና ጫና ብቸኛ ተጠቂ ያስመስለዋል፡፡ ሌሎቹም በተናጠል ..እሱን.. መሆናቸውን ይዘነጋል፡፡ እነሱ እና እሱ ደግሞ ብቻውን የተነጠለ የመከራ ሰለባ ያደርጋል፡፡ በተናጠል ማንንም የሚያጋጥም ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ብቻውን የወደቀ ይመስለዋል፡፡ ብቻውን በራሱ ውስጥ ስለወደቀ የራሱን ስሜት እንጂ ከበስተውጭ ያለውን እውነታ ማገናዘብ ይሳነዋል፡፡ በራሱ መታወክ ውስጥ መውደቅ የሚያስከስተውን ስቃይ ለመገላገል የህይወትን ግዛት ይጥሳል፡፡
የግለሰቡን ዋና ዋጋ (ህይወት) የሚያስጠፋውም ማህበረሰቡ ነው፡፡ የሚያድነው ግን ግለሰብን ሌላ ግለሰብ ነው፡፡ ግለሰብ የማህበረሰብ መስዋዕት መሆን የለበትም!   
ለማንኛውም ..ራስን ማጥፋት ይፈቀዳል ወይንስ ክልክል ነው፤ ይደገፋል ወይንስ ይወገዛል.. . . . ቢደገፍም ቢወገዝም ራስን ማጥፋት ድሮም ሆነ ዘንድሮ በዙሪያችን ያለ እውነታ ነው፡፡ ከዙሪያችንም ይበልጥ በውስጣችን በግለሰብ ላይ ያሉ ዘርፈ ብዙ የሞራል ቀውሶችን ያውም ተመስሎ፡፡

ምንጭ አዲስ አድማስ

 

About the Author