ትኩሳት የስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ወጣትነት ትውስታ ድርሰት፦
ስብሐት በወጣትነቱ፣ ስብሐት በስርጅናው ስዕሎቹ እታች ይታያሉ፣ ስብሐት ወጣትነትን እንደሚያደንቅ ሁሉ እርጅናን ይፈራ ነበር፣ እርጅና ቃሉ ያሸማቅቀዋል። በፈረንሣይ ሀገር የ፪ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት በየቦታው የፈረንሣይ ሴትና ወንድ አዛውንቶች ያጋጥሙታል፣ የእርጅናንም አስፈሪነት ያስገነዝቡታል፤ ስብሐት ይህንን በትኩሳት መፅሐፉ እንዲህ ይገልፀዋል፦
" በጣም ይቀፋሉ የፈረንጅ ሽማግለዎችና አሮጊቶች። ጨምዳዳ ቆዳቸው የተሰነጣጠቀ ደረቅ ሠም ይመስላል። ቀጥቃጣዎች። ዝምተኞች። አገጫቸው ተገንጥሎ ወደ ታች የወደቀ፣ ከንፈራቸው የተንጠለጠለ፣ ጥርሳቸው የፈራረሰ ሽማግሌዎች። ጥርሳቸው አልቆ አፋቸው ወደ ውስጥ የጎደጎደ ፅማም አሮጊቶች። የመኖር ግዜያቸው አልፎ የሞት ግዜያቸውን ዘመናዊ ህክምና ከልክሏቸው ፣ ታችኛ ከንፈራቸውን እንደ ጡጦ እየጠቡ ሞትን ሲጠብቁ የሚውሉ የሕይወት ኦናዎች። ለዓይን ብቻ ሳይሆን ለአፍንጫም ይቀፋሉ ። የልዩ ልዩ መድኃኒት ፣ የእርጅና፣ የሞት ሽታ፣ ሳይቀበር መግማት የጀመረ ሥጋ።"
ለስብሐት አስፈሪው እርጅና እንደዚያ ነበር የሚታየው፣ አበስኩ ገበርኩ የሚያሰኝ፣ ተላላፊ በሽታን የመሠለ። ወጣትነትስ? እንዲህ ይገልፀዋል፦
" ጥሩ ነው ወጣት መሆን ገንዘብ ባይኖርህም ጤና ይኖርሀል፣ መልክ ባይኖርህም አንጎል ይኖርሀል፣ ዕውቀት ባይኖርህም ጉራ ይኖርሀል፣ ፍቅር ባይኖርህም ተስፋ ይኖርሀል፣ ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሀል፣ መጨቆን ቢኖርብህ ሪቮሉሽን ታነሳለህ-------መኖር ቢያስጠላህ ወይም ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ፣ ሠው ባያውቀም ቅሉ ታሪክ ይኖርሀል ወጣት ነህና።"
ወይ ጋሽ ስብሐት የሚገርም ነው። እስቲ የንዴት መኖር፣ የጉራ መኖርና ራስን መግደል እንዴት እንደ መፍትሔ ሀሳብ ይቆጠራል። ምናልባት የወጣትነት ድፍረትና ቆራጥነት እነዚህንም እንደ መፍትሔ ሀሳብ ያስቆጥር ይሆን።
ጋሽ ስብሐት በትኩሣት መፅሐፉ ብዙ ነገር ይላል፣ በብዙ ነገር ይፈላሰፋል፣ በፈረንሳይ ተማሪ በነበረበት ግዜ ማነሁለል ይችልበት ነበር፣ ከቆነጃጅት የፈረንሳይ እንስት ወጣቶች ጋር ዓለሙን ቀጭቷል፣ በቋንቋው ያነሆልላል፣ ዐዕምሮው ለዕውቀት ክፍት ነበር፣ በጥቂት ግዜ የፈረንሳይኛ ቋንቋን በቁጥጥሩ ስር አድርጎት ነበር፣ ችሎታው በዛዚ ርዕስ የንኮሎንመፅሐፍ በአማርኛ እንዲተረጉም አብቅቶታል፣ ጨዋነቱ፣መልከ መልካምነቱና ከፍተኛ የቀለም ቀበኛነቱ ተወዳጅነትን አትርፎለት ነበር።
የምትወደውንና መልከመልካሟን ፈረንሣይት ወጣት እንዲህ ይገልፃታል፦
" ሲልቢ በጣም ቆንጆ ናት፣ እጥር ምጥን ያለች ፈረንሳዊት ሆና ቡናማ ጉልህ አይኖችዋ ውስጥና ውብ አፍዋ ዙሪያ እንደ ነበልባል የሚውለበለበው ፈገግታዋ ልብ ያሞቃል። ወደ ኋላ የተለቀቀው ንፁህ ጥቁር ፀጉሯ ያብለጨልጫል ------ከታች ደግሞ አበጥ ያለው ዳሌዋ እንደ ፀጉሯ ይወዛወዛል። እግርዋ በብዙ ጥንቃቄ የተቀረፀ ውብ ፍጥረት ነው። ፍቅርም ምቾትም የምትቀሠቅስ ወጣት ትመስላለች።"
ስብሐት ቀላል ሠው አልነበረም። በሲልቢ እጅግ በጠም የሚወደድና የሚፈቀር ወጣት ነበር። በመፅሐፉ እንደተገለፀው የስብሐት ጨዋነትና በራስ ላይ የነበረው ዕምነት፣ ደንታ ቢስነት ብዙም ለሴትም ሆነ ለሌላ አለመጨናነቅ በሲልቢ ተወዳጅ አድርጎታል። ባይታወቅበትምና በድብቅ ቢይዘውም ቅብጥብጥ ወጣቷን ማፈቀሩና እንደምታስቀናውም በመፅሐፉ ገልጿል።
ባጠቃላይ ትኩሳት መፅሐፉ ትኩስ ጉልበት ስላለው የወጣቶች ከስብሐት ስራዎች ቀዳሚ ምርጫ መሆኑን ብዙ ወጣቶች ያወሳሉ።
በዚህ መፅሐፉ ስብሐት ስለ ፍቅርና ቅናት ተቃርኖና ጥምርታዊ ግንኙነት፣ ገፅታን ስለማንበብ፣ ስለ ሪቮሊሲዮን፣ የወጣትነትና አዛውንትነት የሕይወት ሂደት፣ የሴት ልጅ ውበትና መስህብነት፣ የፍቅር ሳይኮሎጂ፣ የቋንቋ ክህሎት ጠቀሜታ፣ ሠውን ከእንስሳት የሚለዩ ሠብአዊ ባኅሪያት፣ የወጣትነት ትርጉምና መገለጫዎቹ፣ ግዜን ስለ መመንዘርና መጠቀም፣ ምሳሌያዊ አገላለፆች፣ ስለ ጭቡና ጭቆናንም አካቶ በሚያስደምም ሁኔታ ከሽኖ አቅርቧል።
በስዕሉ ላይ የወጣትነትና የስተርጅና ሥዕሎች ይታያሉ፣ ጋሽ ስብሐት የጠላውና የተቸው ዕርጅና መጥቶ እፊቱ ገጭ አለ።
#ምንጭ:- ጌታቸው ባጫ ከ መጽሃፍ ትሩፋት
Product Details
Synopses & Reviews
ትኩሳት የስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ወጣትነት ትውስታ ድርሰት፦
ስብሐት በወጣትነቱ፣ ስብሐት በስርጅናው ስዕሎቹ እታች ይታያሉ፣ ስብሐት ወጣትነትን እንደሚያደንቅ ሁሉ እርጅናን ይፈራ ነበር፣ እርጅና ቃሉ ያሸማቅቀዋል። በፈረንሣይ ሀገር የ፪ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት በየቦታው የፈረንሣይ ሴትና ወንድ አዛውንቶች ያጋጥሙታል፣ የእርጅናንም አስፈሪነት ያስገነዝቡታል፤ ስብሐት ይህንን በትኩሳት መፅሐፉ እንዲህ ይገልፀዋል፦
" በጣም ይቀፋሉ የፈረንጅ ሽማግለዎችና አሮጊቶች። ጨምዳዳ ቆዳቸው የተሰነጣጠቀ ደረቅ ሠም ይመስላል። ቀጥቃጣዎች። ዝምተኞች። አገጫቸው ተገንጥሎ ወደ ታች የወደቀ፣ ከንፈራቸው የተንጠለጠለ፣ ጥርሳቸው የፈራረሰ ሽማግሌዎች። ጥርሳቸው አልቆ አፋቸው ወደ ውስጥ የጎደጎደ ፅማም አሮጊቶች። የመኖር ግዜያቸው አልፎ የሞት ግዜያቸውን ዘመናዊ ህክምና ከልክሏቸው ፣ ታችኛ ከንፈራቸውን እንደ ጡጦ እየጠቡ ሞትን ሲጠብቁ የሚውሉ የሕይወት ኦናዎች። ለዓይን ብቻ ሳይሆን ለአፍንጫም ይቀፋሉ ። የልዩ ልዩ መድኃኒት ፣ የእርጅና፣ የሞት ሽታ፣ ሳይቀበር መግማት የጀመረ ሥጋ።"
About the Author
በስብሃት ትግራይ ጠቅላይ ግዛት በአድዋ አውራጃ ርባገረድ በምትባል መንደር ከ አቶ ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ዮሐንስ እና ከ ወይዘሮ መዓዛ ተወልደ መድህን በ ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ተወለደ ። በኢትዮጵያ ስነጽህፍ ጉልህ አሻራ ትቶ ያለፈ ጸሃፊ ነው።
ስብሃት ከአንድ ወጣት ጋዜጠኛ ጋር እየተጨዋወተ ነው። ጋዜጠኛው ስብሃትን ይጠይቀዋል። " በአዲስአበባ ውስጥ ስብሃቲዝም የሚባል እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ሰምተዋል ወይ ?"ይለዋል ጋሽ ስብሃትም ሲመልስ "እንግዲህ ስብሃት ማለት ከላይ ከሚለብሰው ሱሪ ስር ቀጠን ያለች ቱታ የሚለብስ ሲሆን ፤ ይህንንም የሚያደርገው ለፋሽን ሳይሆን ቁርጥማት ስላለበት ራሱን ከብርድ ለመከላከል ነው። ደግሞም ከማህበረሰብ ጋር እየኖረ ፤ የማህበረሰብን ልምድ ሳይንቅ ፈንጠር ብሎ
በትዝብት ይስቃል። ይህንን ከሆነ ስብሃቲዝም
የሚሉት። ይመቻቸው ። ይከተሉት። "
በእርግጥ ስብሃቲዝም የሚባል እንቅስቃሴ ተጀምሮ ነበር። ይሄ አስተሳሰብ በግልፅ ቋንቋ ተብራርቶ ስብከት ባይደረግበትም ብዙ ተከታዮችን ሊያፈራ የቻለ ነበር። አብዛኛው ተከታዮቹ ደግሞ ወደ ጥበብ አለም ጠጋ ያሉ ሰዎች ናቸው። ጀማሪ ጋዜጠኞች ፤ቲያትረኞች ፤ መፅሀፉቸው እንዲገመገምላቸው የሚፈልጉ ደራሲያን ወደ ስብሃት ጠጋ ብለው ፤ ከእግሩ ስር ቁጭ ብለው ይማሩ ነበር። ስብሃት ሲሰብክ ይሰማሉ ፤ ዕድል ሲያገኙ ደግሞ ግር ያላቸውን ነገር ይጠይቃሉ።
ስብሃቲዝም ለኢትዮጵያ ስነ-ጥበብ የበዛ አበርክቶት የሰጠ ነው። አሁን በኢትዮጵያ የስነ-ፅሁፍ ታሪክ ውስጥ የፊት መስመሩን የያዙትን ደራሲያን የወለደልን ስብሃቲዝም ነው።
#ምንጭ:- ካሌብ ገብረ ኪዳን ከ መጽሃፍ ትሩፋት ምንጭ ዘነበ ወላን ያጣቀሰ
የሰጠን የስብሃቲዝም መንገድ ፤ ግምገማና ሂስ ነው።
ከስብሃት የቅርብ ጓደኛ ከነበረ ደራሲ ጋር ስናወራ
ስለ ስበሃቲዝም ተፅዕኖ እንዲህ ነበር ያለኝ " አሁን
ሲወራ ቀላል ይመስላል እንጂ ስብሃቲዝም ቀላል
ሙቭመንት አልነበረም። ስራህን ኑሮህን ትተህ
እንድትከተለው ያስገድድህ ነበር። "
ከተለያዩ ጽሁፎች በትንሹ ቀነጫጭበን እንሆ
ከዕለታት አንድ ቀን ጋሼ ስብሃት በከተማ አውቶቢስ ይጓዛል። አንድ ሌባ ጠጋ አለና ኪሱ ገባ። ጋሼ ስብሃት ቀድሞ ነቅቶ ኖሮ "ምነው!" አለው። ሌባውም ደንገጥ ብሎ "ውይ የኔ ኪስ መስሎኝ ነው" ሲል መለሰለት።
ጋሼ ስብሃት የሚወርድበት አከባቢ ሲደርስ እየተራመደ ሌባውን ጭው አደረገው። ሌባውም ምነው ሲለው "ውይ የኔ ፊት መስሎኝ ነው" አለው።