ፌላሌምሌሞንም - yabeto

ፌላሌምሌሞንም

Regular price
$3.17
Sale price
$3.17
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

ፌላሌምሌሞንም
ከማኢጎ ጉቤ
እነዚህን ደብተራዎች አልቻልናቸውም። ማኅሌቱ አይቀራቸው፤ ስብከቱ አይቀራቸው፤ ትርጓሜው አይቀራቸው ሁሉንም ይዘውታል። ወንበር ተክለው ያስተምራሉ፤ ዓውደ ምሕረት ቆመው ይሰብካሉ፤ ሱቅ ስንገባ መጽሐፍ ሆነው ተደርድረው እናገኛቸዋለን።
ዛሬም ዓራት ዓይናው ሊቅ፣ የትርጓሜው ባለቤት፣ የትሕትናው ጌታ በመጽሐፍ መጣሁላችሁ እያሉን ነው። የአቡሻኽርን ውቅያኖስ በሚመጥነን ኩሬ ወስነው ሰንደውታል፤ አነጋጋሪውን ሣልሳዊ ቴዎድሮስን ቁልጭልጭ አድርገው ከትበውታል። ኪናዊ ቃላትን በየዓረፍተ ነገሩ ሰካክተው ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ሥለውበታል። መቼትና ገፀ ባሕሪ፣ ታሪክና እውነት ተዛዝለው ሕያው ሆነው ቀርበውበታል። ልቦለድ እንዳይሉት ያልተደፈረን እውነት ደፍረዋል፤ ደረቅ ታሪክ እንዳይሉት ኪነ ጥበብ በመጽሐፉ ውስጥ ግዘፍ ነስታ ወዲያ ወዲህ ስትል ያዩበታል። በየመጻሕፍት ቤቱ እየገዛችሁ አንብቡ።
ደራሲው ማን ነው ብላችሁ እንዳትጠይቁኝ! ከዚያው መጽሐፉ ላይ ከማኢጎ ጉቤ ተብሎ ተገልጿል።
ምንጭ ታደለ ሲሳይ

Product Details

አቡሻኽር - የጊዜ ቀመር: መንፈሳዊ እና ሳይንሳዊ የጊዜ ትንተናዎች - የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ድንቅ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከመሠረቱ እስከ ጉልላቱ -- ከፍጥረተ ዓለም እስከ ኅልፈተ-ዓለም - በመጽሐፍ ቅዱስ የጊዜ መስመር።
የ13ኛ ወራችን የጳጉሜን አስገራሚ የጊዜ ቀመር - እስከ 7ኛዋ የጳጉሜን ቀን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጽዋማትና በዓላት ስሌት /ባሕረ ሃሳብ/
ዛሬም ዓራት ዓይናው ሊቅ፣ የትርጓሜው ባለቤት፣ የትሕትናው ጌታ አባታችን መምህራችን ፌላሌምሌሞንም በሚል ድንቅ መጽሐፍ መጣሁላችሁ እያሉን ነው።
ኢትዮጵያ ዘወትር እንደሚወሳው ዝንተ ዓለም እንደሚጠቀሰው ለየት ያሉ መለያዎች አሏት ከሚያስብሉት መካከል የዘመን አቆጣጠሯ አንዱ ነው፡፡ ከመደበኛው የዘመን መቁጠርያዋ በተጨማሪ እንደየኅብረተሰቡ ባህልና ሃይማኖት የተለያዩ የዘመን መስፈሪያዎች አሏት፡፡
በተጨማሪ ንጉሥ ቴዎድሮስ ስለሚባለው ደግ እና ጸሎተኛ ባሕታዊ የወደፊት በኢትዮጵያ ትንሣኤ ውስጥ የተቀባ እና የኢትዮጵያ ትንሣኤ መሪ እና አብሳሪ ስለሆነው ንጉሥ ይነግረናል ።
ለምሳሌ ስለ ኢትዮጵያ ትንሣኤ ብቻ በፍካሬ ኢየሱስ፣በድርሳነ ዑራኤል፣በገድለ ፊቅጦር፣በገድለ አቡነ ሲኖዳ፣በራዕየ ሳቤላ፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በጻፉት በመጽሐፈ ምስጢር እና በትሮጓሜ ወንጌል ላይ ይገኛል። እንዲሁም እዚህ መጽሐፍ ላይ ሣልሳዊ ቴዎድሮስን ቁልጭልጭ አድርገው ከትበውታል።

Synopses & Reviews


እኛ ኢትዮጵያዊያን ያጣነው ሃብት ወይም ዕውቀት ወይም ጥበብ አይደለም፣ ሰው ነው ያጣነው ።
ሌሎች ኢትዮጵያን የመሰሉ ሃገራት ደሃ ሁነው የቀሩት በሃይማኖት ሰበብ በእርዳታ ስም የሚንቀሳቀሱ ፈረንጆችን ከልብ በቅንነት አምነው ወደ ሃገራቸው በማስገባታቸው ማንነታቸውን ሃይማኖታቸውን እና የምስጢራቸውን ቁልፍ ካስረከቡ በኃላ ነው። ኢትዮጵያ ግን በቀደምት አባቶቻችን መሪር ተጋድሎና መስዋዕትነት ነፃነቷን እና ክብሯን ብቻ ሳይሆን ምስጢራዊ ሀብቷንም (ጥበብና ዕውቀት) ጭምር ጠብቃ የቆየችው በተለያዩ ጊዜ ሊወሯት ለመጡት ፈረንጆች የበሯን መክፈቻ አሳልፋ ባለመስጠቷ ነው። ይህችን ሃገር ለማጥፋት ብዙ መርዛማ ዕቅዶች ታቅዶላት ብዙ ሰይጣናዊ ተልዕኮዎች የተላከባት ሃገር ነች። ሁሉም ግን ከሽፈዋል። ከዚህ በፊት በተለያየ መንገድ ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ብዙ ሙከራዎች ተደርገው ነበር። ረቂቅ ሴራዎች ተጠንስሰው ነበር። ግን ዛሬም ወደፊትም ከየትኛውም ዓለም የሚደረጉ ኢትዮጵያን የማጥፋት ሙከራዎች ሴራዎችና ተንኮሎች መቼም ቢሆን አይሳኩም። ሃገራችን በ24ቱ ካህናተ ሰማይ የምትጠበቅ ልዩ ሃገር ናትና።
ኢትዮጵያን የውስጥ እንጅ የውጭ ጠላት እንደማያጠፋት ነገሩ የታመነ ነው።
ድሮም ከዚች ሃገር ላይ ወደ ስልጣን የሚወጡ ሰዎች ውድቀታቸውና ውርደታቸው የሚጀምረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሲዳፈሩ ነው።

About the Author