ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬን ለአንቺ - yabeto

ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬን ለአንቺ

Regular price
$2.53
Sale price
$2.53
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

ክዋክብታማ ሰማይ ለማየት መድፈሩ። የመጀመሪያዎቹ ገፆች ላይ ያሉት የትዝታ ቁርጥራጮች፣ እንደተቦዳደሰ ዘመናዊ ጂንስ የትውልድ ጭርንቁስ ጥፈትን የሚወክሉ መስሎኝ ነበር። ትንሽ የከረመ ፔሲሚዝም አለብኝ።
በቫንጐ “Starry night” ተመስረኩዞ የመጣ ሌላ አጭበርባሪ ነበር የመሰለኝ። ምንም አዲስ ትርጉም ሲጠፋ፣ የምንምን ፍቺ ጥልቅ ለማስመሰል ከሚታሹት መሀል ነበር ይሄም መጽሐፍ መጀመሪያ የመሰለኝ። ትዝታ ቅንጭብጫቢ ስለሆነ፣ በቅንጭብጫቢ ድረታ ደረቴን ሊረግጠኝ መስሎኝ ነበር። ደግሞም፣ የመጀመሪያዎቹ አንቀፆች ላይ በነጠላ ሰረዝ አንድን ነገር ለመግለጽ የሚጨነቅባቸው ገፆች እውነትም ግልጽ አልነበሩም። ጭቶ እያከኩ አንድ ስፍራ ላይ ቆመው ወደፊት መራመድ አቅቷቸው ከሚብሰለሰሉት መሃል ግን አይደለም እሱባለው። እሱባለው እና እሱ እንዳለው የተፃፈው መጽሐፉ።
ቀስ እያለ ነው ውበት የሚገለፀው። እንደ ኪዩቢዝም የተጣፉ የሚመስሉት ትዝታዎች በኋላ ላይ እየተሳሰሩ መምጣት ይጀምራሉ። ልክ እንደ ተፈጥሮ። ልክ እንደ "Butterfly effect” የቀደመው የድርሰቱ ገፆች ላይ የአተበው ትዝታ ውጤቱ በሂደት ነው የሚታወቀው። ነጣጥሎ ትዝታዎቹን ባያሳይ ለካ ሲገጣጠሙ ወጥ ምስል ባልፈጠሩ ነበር! እውነታ ከቁርጥራጭ “ከፒክስሎፕ” እንጂ ከወጥ ሽመና ተመዞ የሚዘረጋ አይደለም ለካ!

Product Details

Synopses & Reviews

"የጥበብ ሰማይ ሊታረቅ ሲፈልግ ምልክቱን ያሳያል"
ኂሳዊ ንባብ ፡ በደራሲ ሌሊሣ ግርማ
(በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነሐሴ 9 ቀን 2012 ዓ.ም እንዳስነበበው)
እስክሪብቶዬን ያነሳሁት በሁለት እጄ ነው። ላንስሎት በድንጋይ ውስጥ ተሽጦ የኖረውን ምትሃታዊ ሰይፍ በሁለት እጁ መዞ እንዳወጣው። እያካበድኩ ሳይሆን የእውነት ብዕር ማንሳት እየከበደኝ መጥቶ ነበር። ዲጂኖ እንደ ማንሳት ወይም ብቅል ለመውቀጥ ሙቀጫ እንደ ማንሳት ተራ ጉዳይ እየመሰለኝ አሰልችቶኝ ነበር። በብዕር አካፋ ፊደል እንደ ማፈስ ዝም ብሎ እጅ መላጥና እጅ ተልጦ የሚፃፈውም ነገር የአንባቢውን ጨጓራ ከመላጥ የማይዘል እየሆነብኝ ስለመጣ ብዕር መሰንዘር እየከበደኝ መጥቶ ነበር።

ጠቢባኑ ተስማሙም አልተስማሙም፣ የሆነ ነገር ብልጭ ብሏል። ከብልጭታው ውስጥ የመብረቅ ብረት መፈለግ ወይም አደገኛ ሞገድ ነው ብሎ በሽቦ ወደ መሬት ማሳ አድርገው መቅበር የእነሱ ምርጫ ነው። ማክበርም መድፈርም ይችላሉ። አፈጣጠሯ የሚገርም አንድ ለየት ያለች ውበት ግን ከየት እንደመጣች፣ በምን ግፊት እንደመጣች ሳትታወቅ በአደባባይ እያለፈች ነው። እንደ ዶሮ እንቁላል፣ በተፈጥሮ ችሮታ ድንገት የተጣለች ሳይሆን፣ ተሰጥኦና ማስተዋል ታክሎባት የተገኘች መሆኑን ሳስብ፣ በአክብሮት አንገቴን ዝቅ አደርጋለሁ:: መጽሐፉን ማንበብ ለሚፈልግ አሳልፌ እሰጣትና እኔ ግን በልቦናዬ አስቀምጣታለሁ።

About the Author