የግብፅ እና አጋሮቿ ጠላትነት እስከመቼ?

የግብፅ እና አጋሮቿ ጠላትነት እስከመቼ?

Regular price
$6.40
Sale price
$6.40
Regular price
Sold out
Unit price
per 
Shipping calculated at checkout.

የግብፅና አጋሮቿ ጠላትነት እስከመቼ?
#Ethiopia | መቅድም (ስለመጽሐፉ አጭር መግለጫ)
ዛሬ በአገራችን “ኢትዮጵያ የምትባል አገር አልነበረችም፣ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረችው በዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ ዘመነ-መንግሥት ነው፡፡” ወዘተ የሚሉ ህወኃቶችና ሌሎች የህወኃት አምላኪ ጽንፈኞች አሉ፡፡ ጽንፈኞች ምንም ይበሉ ምን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ40 ጊዜ በላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ 51 የአፍሪካ አገሮች ሳይፈጠሩ መላዋ አፍሪካ ኢትዮጵያ፣ የዛሬው አትላንቲክ ውቂያኖስ ደግሞ የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ተብሎ ሲጠራ እንደነበር አያሌ የታሪክ ፀሐፊዎች ከፃፉት በተጨማሪ የተለያዩ ጥንታዊያን አሳሾች ከነደፏቸው ተጨባጭ ካርታዎች ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከዚህ በታች የተመለከተውን በቅርቡ በጄ.ኤ. ሮጀርስ እ.አ.አ. በ1650 የተሠራውን ካርታ ይመልከቱ፡፡
ጥያቄው ይህን እውነተኛውን የጥንታዊ ታላቅነት ታረክ ማስቀጠል ወይስ የዚህ አኩሪ ታሪክ ጠላቶች ባስታጠቋቸው ጽንፈኛ ኃይሎች የፈጠራ ታሪክ ተረት፣ ተረት ትርክት ለሩቅም ለቅርብም የጎረቤት ጠላት ተጋልጠን አገር አልባ መሆን ይሻለናል የሚለው ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ጽንፈኛ አካል ድንገት ተነስቶ ሊያጠፋቸው የማይችላቸው አራት የኢትዮጵያ መሠረቶች አሉ፡፡ እነዚህም፡- የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ፣ ኢትዮጵያዊነትና የኦርቶዶክስና የእስልምና ኃይማኖኖቶች ናቸው፡፡ እናም ኢትዮጵያ ለሺዎች ዓመታት ነበረች፣ አለች ወደፊትም በጀግኖች ልጆቿ ደምና አጥንት ታፍራ፣ ተከብራና ኮርታ ትኖራለች፡፡
ይህ የግብፅና አጋሮቿ ጠላትነት እስከመቼ? (ከግድቡ እርሾዎች) የተሰኘው መፅሐፍ የተፃፈው በፊት ለፊት የሽፋን ገጹ ላይ በተመለከተው አረባዊ አባባል መነሻነት በዚህ መፅሐፍ ባላገሩ በሚል የብዕር ስም በሚታወቅ ኢትዮጵያዊና በዚሁ አረባዊ መካከል በተለይ ከ1983 ዓ/ም በፊት የነበረውን የኢትዮ-ሻዕቢያና ህወኃት ጦርነት በተመለከተ በባዕድ አገር ዩንቨርስቲ ውስጥ በተደረገ ለ5 ዓመታት የዘለቀ እጅግ እልህ አስጨራሽ ፍትጊያ እውነተኛ ታሪክ መሠረት በማድረግ ነው፡፡
በአጭሩ የመካከለኛው ምሥራቅና የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ጂኦፖለቲክስ ችግርን በተለይ ከኢትዮ-ሻዕቢያ እና ህወኃት ጦርነት ጋር ተያይዞ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ላይ በመመሥረት የተፃፈ ነው፡፡ መፅሐፉ የኢትዮጵያን ችግር በሚገባ ተገንዝበው የመፍትሔ አካል ለመሆን ለሚሹ ዜጎች፣ ለዓባይ ተፋሰስ አገሮች ግንኙነት ታሪክ ተማሪዎች፣ ምሁራንና ተመራማሪዎች፣ ለመካከለኛው ምሥራቅና አፍሪካ ቀንድ ጂኦፖለቲክስ ችግር መፍትሔ አፈላላጊ ወገኖች የሚጠቅም ግብዓት እንዳለው ይታመናል፡፡
የመፅሐፉ ዋና ዓላማ ከፍ ብሎ በአንደኛው አንቀጽ የተመለከቱት የአገራችን ችግሮች መላው የአገራችን ሀዝቦች በተለይ ቢያንስ ለ30 ዓመታት በተሳሳተና በአንድ ዘር ጥላቻ ላይ ተመሥርቶ በእጅግ አገር አጥፊ የፈጠራ ታሪክ ትርክት የተበረዘው ትውልድ የአገሩን መሠረታዊ ችግሮችንና መፍትሔዎቻቸውን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ወዳጆችና ጠላቶችን ለይቶ አውቆ የችግሩ አካል ከመሆን ወጥቶ የመፍትሔው አካል እንዲሆን ለማስቻል ታስቦ የተፃፈ ነው፡፡
ይህን ዓላማ ለማሳካት ሲባል በመፅሐፉ ውስጥ የአንጋፋ ፓርቲ መሪዎች ከልጅነት እስከሽበት ያመከኗቸው መልካም አጋጣሚዎችና ዕድሎች እንዲሁም የፈጸሟቸው ስህተቶች፣ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ ሶማሊያና ግብጽ ታሪክ አጫጭር ማስታወሻ፣ ባላገሩና የግድቡ እርሾ ከግድቡ ዋዜማ፣ የአፍሪካ ቀንድና የመካከለኛው ምሥራቅ ጂኦፖለቲክስ ቅኝት፣ ከግብፅና ዓባይ ጋር ለተያያዙ ችግሮች ሁሉን አቀፍ ዋና ዋና የመፍትሔ ሀሳቦችና የባላገሩ ማጠቃለያ ወዘተ በሚሉና በአያሌ ሌሎች ተገቢ ዝርዝር ታሪካዊ ሰነዶች ጥናት ላይ በመመሥረት ተጽፏል፡፡
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች የጠነከረ ዲሞክራሲያዊ የአንድነት/አብሮነት መንግሥት ለህግ የበላይነትና ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላም፣ እኩልነት፣ ለአገራችን ደህንነትና ሉአላዊነት፣ ልማትና ዕድገት ብሎም ብልጽግና ብቸኛ ዋስትና መሆኑን ለዚህ መፅሐፍ መፃፍ መሠረት የሆነው የኢትዮጵያና አካባቢዋ ጥናት ውጤት አመላክቷል፡፡

Product Details

Synopses & Reviews

About the Author

የፀሐፊው የረዳት ፕሮፌሰር (ዶ/ር፣ ኢ/ር)
ጥላሁን ኤርዱኖ አጭር ታሪክ
ዶ/ር ጥላሁን ኤርዱኖ ከአባታቸው ከአቶ ኤርዱኖ ሐንቄቦ፣ ከእናታቸው ወ/ሮ ወርቅነሽ ወ/ማሪያም በ1958 ዓ/ም በቀድሞ አጠራር ከምባታና ሀዲያ አውራጃ፣ ኮንተብ ወረዳ፣ ጊዳሻ ቀበሌ ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ በጌጃ ከተማና በናፋጋ ቅዱስ ገብሬኤል መንፈሳዊ ትምህርት የቀሰሙ ሲሆን፣ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመራቢቾ 1ኛ/ደ/ት/ቤት፣ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞርሲጦ መ/2ኛ/ደ/ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዋቸሞ አጠቃላይ/2ኛ/ደረጃ ት/ቤት ተምረዋል፡፡
ለከፍተኛ ትምህርት የሚያበቃ ውጤት በማምጣት በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በጂኦግራፊና ታሪክ ትምህርት ተመርቀው ከ1976-1978 ዓ/ም ለ3 ዓመታት በኮረም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ በ1978 ዓ/ም መጨረሻ የውጭ አገር ትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው ወደ ቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት/ራሺያ-ሞስኮ በማቅናት በካርታ ሥራ ምህንድስና ለ6 ዓመታት ትምህርታቸውን ተከታትለው በ1984 ዓ/ም ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ለዚህ መፅሐፍ መፃፍ ዋነኛ እርሾ የሆነው ምክኒያት ያገኙት በዚሁ ውጭ አገር ትምህርት ቆይታቸው ወቅት ነው፡፡
ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ህወኃት/ኢህአዴግ በዩንቨርስቲ ምሩቃን ላይ የያዘውን ቂም አዘል አቋም ሲቃወሙ ቆይተው በደቡብ መስተዳድር ውኃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የቅየሳና ካርታ ንድፍ ክፍል ኃላፊ በመሆን ለ4ዓመታት አገልግለው ሲያበቁ በ1990 ዓ/ም በቀድሞ የናዝሬት የቴክኒክ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፣ ቀጥሎ ደግሞ በአዳማ ዩንቨርስቲ በመምህርነትና ዲፓርትመንት ኃላፊነት አገልግለዋል፡፡ በ1997 ዓ/ም ለ3ኛ ዲግሪያቸው ተመልሰው ራሺያ በመሄድ የ PhD ትምህርታቸውን በ(School Atlas Cartography) አጠናቀው በ2000 ዓ/ም ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ማስተርስ ፕሮግራም መምህርና የመመረቂያ ጽሑፍ (ቴሲስ) አማካሪ ሆነው አገራቸውን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ከማስተማር ሥራ ጎን ለጎን የዩንቨርስቲው የምርምርና ህትመት እንዲሁም የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቢሮ ዳይሬክተር፣ የሲቪል ኢንጂነሪንግና አርክቴክቸር ት/ቤት ዲን በመሆን አገልግለዋል፡፡ በግላቸው አራት የምርምር ጽሑፎችን በተማሩበት ዩንቨርስቲ ጆርናል ለህትመት አብቅተዋል፡፡
ከዚህ ሁሉ በተጓዳኝ ለሦስት ተርም በመመረጥ የኢትዮጵያ ቅየሳ ምህንድስና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን፣ ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ የታፈነው የሲቪል ማህበራት ህግ እስኪሻሻል ድረስ ለ7 ዓመታት የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና የሙያ ማህበራት ቦርድ አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡ ዛሬም በጠ/ሚሩ የሚመራው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ቴክኒካል ኮሚቴ አባል እና የህደሴ ግድብ ሞዴል አዲስ አበባ ፓርክ ግንባታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል በመሆን አገራችውን በታማኝነትና በቅንነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ለእነዚህና ሌሎች ያልተጠቀሱ ተመሳሳይ ሥራዎቻቸውና አስተዋጽኦዎቻቸው ከግምት ገብቶ ለቅን አገልግሎታቸው የህይወት ዘመን እውቅና በመስጠት በግላቸው ሜዳሊያና ሰርተፊኬት፣ ለሚመሩት ማህበር ደግሞ ዋንጫ ለመሸለም በቅተዋል፡፡
ዶ/ር ጥላሁን ኤርዱኖ በፓርቲ ሳይታቀፉ ውጭ ሆነው በአንድ ታላቅ የአገሪቱ ህዝብ ጥላቻ ላይ የተመሠረተውን አግላይና አድሏዊ የህወኃት/ኢህአዴግን የዘር ፖለቲካ ሥርዓት ሲቃወሙ ቆይተው ዛሬ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን በመቀላቀል በደቡብ መስተዳድር በኮንተብ 01 ምርጫ ወረዳ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ በመሆን ህዝባቸውን ለማገልገል በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡